በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታላቁ ማክሰኞ /Super Tuesday/ የቅድመ ምርጫ ሂደት ሲገመገም


በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራት ፓርቲ ተፎካካሪዎች (የቅድመ ምርጫ ሂደት) በዘጠኝ ግዛቶች አሸናፊ የሆኑት የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከተጠበቀው በላይ ድል ተጎናጸፈዋል።

“..እናም 'ሱፐር ቲዩስዴይ' - 'ታላቁ ማክሰኞ' ይመጣና ጆ ባይደን ያኔ ያበቃልሃል! ብለውኝ ነበር። ደህና! .. ምናልባትም ለሌላኛው ተፎካካሪ ይሆናል ያበቃለት። እስኪ ይሄን ለቨርጂኒያ፣ ለኖርዝ ካሮላይና፣ ለአላባማ፣ ለቴነሲ፣ ለኦክላሆማ፣ ለአርካንሳስ እና ለሚኔሶታ ሰዎች ይንገሯቸው።” የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን።

በቀደሙት የአራት ግዛቶች ምርጫ የሶስቱን በማሸነፍ የቀዳሚውን ሥፍራ ይዘው የነበሩት የቬርመንት ክፍለ ግዛቱ እንደራሴ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ በተጨማሪ ሶስት ክፍለ ግዛቶች ሲያሸንፉ ከፍተኛ ግምት በሚሰጠውና ውጤቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ባልገባው የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ምርጫም በብልጫ ድምጽ መምራት ላይ ናቸው።

“ለዴሞክራት ፓርቲው እጩነት በሚያበቃው ምርጫ አሸንፈን በዚህች ሃገር ታሪክ እጅግ አደገኛ የሆነውን ፕሬዝዳንት ድል እንደምንነሳ ጥርጥር የለውም።” የቬርመንት ክፍለ ግዛቱ እንደራሴ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ።

በዲሞክራት ፓርቲው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩ መለያ ፉክክር የ14 ግዛቶች ምርጫ የተካሄደበትን የትላንቱን 'የታላቁን ማክሰኞ' - 'ሱፐር ቲዩስዴይ' የምርጫ ሂደት ቅኝት እና የፖለቲካ ምሁር ትንታኔ ከዚህ ያድምጡ።

“የታላቁ ማክሰኞ” ቅኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00
በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ቅድመ ምርጫ ሲገመገም
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:59 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG