ዋሽንግተን ዲሲ —
“በህይወት አንዴ” ሊሰኝ የሚችል ገጠመኝ ነበር መነሻው።
በዚያ ሰሞን ታላቅ ዜና ሆኖ በሰነበተው፤ የኖቤል የሰላም ሽልማት መድረክ የተሰሙ ዜማዎቿ ናቸው መግቢያዎቹ።
አዎን! ሥነ ሥርዓቱ በቀጥታ የቴሌቭዥን በዓለም ዙሪያ በተሰራጨበት ወቅት በዚያ ልዩ መድረክ በተጫወተቻቸው “አገሬ” እና “እወድሃለሁ” በተሰኙት ሁለት ዘፈኖቿ አማካኝነት የኢትዮጵያን ባሕል ለዓለም የማስተዋወቅ ልዩ ዕድል ከገጠማት ከወጣቷ ድምጻዊት ብሩክታዊት ጌታሁን ጋር ያን ልዩ አጋጣሚ ጨምሮ፣ የሙዚቃ ሕይወት መንገዷቿ እና ሌሎች የሙዚቃውን ዓለም በሚመለከቱ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ተጨዋወትን። በተከታታይ ክፍሎች የቀረበውን ወጋችንን ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ