የካይሪፕራክተር ባለሞያ ናቸው። ዶ/ር ሰላም አክሊሉ ይባላሉ። በያመቱ ቁጥራቸው በብዙ ሺህ የሚገመቱ ሰዎችን “አላስቆም አላስቀምጥ” ለሚል ሥቃይ የሚዳርገውን የጀርባ እና የአከርካሪ አጥንቶች ሕመም፤ አስቀድሞ ለመከላከል የሚበጁ መላዎች ያቀፈ ዘመቻ ይዘዋል።
ዶ/ር ሰላም በቅርቡ ወደ ስቱዲዮዋችን ጎራ ባሉበት ወቅት ስለ ያዙት ጥረት እና እነኝህ የሕመም ዓይነቶች በተለይ በካይሮፕራክቲክ ሕክምና መረዳት የሚችሉ በሆኑ ጊዜ ስለሚኖረው ሁኔታ አወያተናቸዋል።
የምልልሳችንን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።