አሥመራ —
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው ቴሌቪዝን ቀርበው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በሀገራቸው እና በኢትዮጵያ መካከል የተጀመረውንና ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ የሆነውን አዲስ ግንኙነት "መልካም ጅምር" እንደሆነ አመልክተው እስካሁን የተከናወነው ሥራ የተፈለገውን ያህል ያለመሆኑን እና ለዚህም ምክኒያት ያሉትን ጨምረው ተናግረዋል።
በሁለቱ ሀገሮች መካከል ለቆዩት ችግሮች ተጠያቂ ያደረጉት የህወሓትን መሪዎች እና "የውጭ" ያሉዋቸውን ኃይሎች ነው። ይሁንና "የውጭ" ያሉዋቸውን ወገኖች ማንነት ግን አላብራሩም።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ