በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ ተዘጋጅታ ይሆን?


ስዌቶ ደቡብ አፍሪቃ ዛሬ- ከተጨናነቀ ባቡር የተሳፈሩ ተጓዦች
ስዌቶ ደቡብ አፍሪቃ ዛሬ- ከተጨናነቀ ባቡር የተሳፈሩ ተጓዦች

አፍሪቃ የኮረናቫይረስን መዛመት ለመግታት የቱን ያህል ተዘጋጅታ ይሆን?

በአህጉር ደረጃ የቫይረሱ ሥርጭት አሁንም ገና በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም፤ አንዴ ከገባ በኋላ ግን በቀናት ውስጥ እየታየ ያለውን የፍጥነት መዛመት ተከትሎ በርካታ የአፍሪቃ አገሮች ወረርሽኙን ለመግታት ልዩ ልዩ ዕርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ አንዳንድ አገሮች ቫይረሱ የደቀነውን ብርቲ ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል የመሰረተ ልማትም ሆነ የቴክኒክ ብቃት የላቸውም።

ይህን ዓለምን እያራደ የሚገኝ ወረርሽኝ የጥድፊያ መዛመት ለመግታት ለመሆኑ አሕጉረ-አፍሪቃ የቱን ያህል ተዘጋጅታ ይሆን?

አፍሪቃ ተዘጋጅታ ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:49 0:00

በወረርሽኙ ብርታት አሁንም ገና ከጅማሬው ደረጃ ላይ ያለችው አፍሪቃ 372 ሰዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው የተረጋገጠባት እና እስካሁን 8 ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸው የተዘገበባት አሕጉር .. ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ቀደም ብሎ ክፉኛ ካጠቃቸውና ካሁን ቀደም ታይቶ የማያውቅ የተባለውን ጨምሮ በፍጥነት በወሰዷቸው እርምጃዎች ከተሳካላቸው አገሮችም ሆነ ካልሰመረላቸው ሌሎች የቱን ያህል ትምሕርት ቀስማ ይሆን? ማድረግ ያለባትን ብቻ ሳይሆን በሰዓቱ ማድረግስ ተችሏት ይሆን? ወይም ጀምራለች?

እስካሁን ከሃምሳ አራቱ አገሮች ከፊል ያህሉ (27 አገሮች) ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች በድንበሮቻቸው ክልል ውስጥ መኖራቸውን በምርመራ አረጋግጠዋል። እናም ያ ቁጥር በየሰዓቱ እየጨመረ ነው።

እስኪ አንዳንዱን እያነሳን የአሕጉሪቱን ይዞታ በወፍ በረር መልከት እናድርግ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG