በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮረናቫይረስ አመጣሽ አዲስ የሕይወት ዘይቤ


Professor Dawd Seid Siraj
Professor Dawd Seid Siraj

የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ ሺዎችን ለሕልፈት ከመዳረግ እና ሌሎች በርካታ ሺዎችን ለሕመምና ስቃይ ከማጋለጥ ባሻገር የሰዎችን የተለመደ የዕለት-ተዕለት የሕይወት ዘይቤም እየቀየረ ነው።

ኮረናቫይረስ አመጣሽ አዲስ የሕይወት ዘይቤ - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:25 0:00


80 ሺህ ሰው ለቫይረሱ ከተጋለጠባትና ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ለሕልፈት ከተዳረጉባት የወርሽኙ መነሻ ከሆነችው ቻይና ቀጥላ ከ9ሺ በላይ ዜጎቿ ለቫይረሱ መጋለጣቸው የተረጋገጡባት እና በወረርሽኙ ጥናት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ጣሊያን የወረርሽኙን ጥድፊያ መዛመት ለመግታት በያዘችው ጥረት የመላ አገሪቱን መግቢያ መውጫዎች እንዲዘጉ በማድረግ የ60 ሚልዮን ሕዝቧን እንቅስቃሴ ገድባለች።

በዩናይትድ ስቴትስም የሁኔታው አሳሳቢነት እያደር እየጨመረ ነው።

በአንጻሩ በአዎንታ ሊታይ በሚችል የተስፋ ጭላንጭል፣ በቻይና ለቫይረሱ አዲስ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። ከአጠቃላዩ ከ110 ሺህ በላይ ሰው ስልሳ ሺው አገግሟል። በጣልያን ለቫይረሱ በመጋለጥ የመጀመሪያው ሰው (ሕመምተኛ ቁጥር አንድ - የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል) ተሽሏቸው ከማገገሚያ ወጥተዋል።

በዚህ ሁሉ በእጅጉ ትኩረት የሚሻ እና አንዳንዴም ግራ አጋቢ ጭምር በሆነ ሂደት ለመሆኑ የወረርሽኙ ቀጣዩ ምዕራፍ ምንድ ነው? እስካሁን ከታየው የሚቀሰም ትምሕርት ይኖር ይሆን? የተዘጋጁትንም ያልተዘጋጁትንም አገሮች ፈተና በባለ ሞያ ዓይን በተከታታይ ለመዳሰስ እንሞክራለን።

ሞያዊ ማብራሪያውን የሚሰጡን ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ፕሮፌሰር እና ከዓለም አቀፍ ጉዞ ጋር የተዛመዱ የሕክምና ጉዳዮች ክትትል ልዩ ክሊኒክ ዲሬክተርም ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG