በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ እንዳይገባ” የጊዜው አሳሳቢ እና አነጋጋሪ ጉዳዮች


ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ እና ዶ/ር ሊያ ታደሰ።
ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ እና ዶ/ር ሊያ ታደሰ።

“አንድ ዕድል ነው ያለን! በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይገባ መከላከል ካልቻልን፤ አንዴ ይሄ ሕመም ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባ የጤና ተቋማቱ አቅቅም የተሟላ ባለመሆኑ - ‘ከገባ በኋላ እንሰራለን’ የሚል ሃሳብ እዚህ ላይ የሚሰራ አይደለም።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ። “ይሄ በሽታ እየጨመረ መሄዱና የአንዳንድ አገሮች ደግሞ ያን የመቋቋም አቅም ጠንካራ አለመሆን በተለይ ለእንደ እኛ ዓይነት አገሮች አሳሳቢ ነው።” ዶ/ር ሊያ ታደሰ።

በቻይና መውጫ መግቢያው በተዘጋባቸው ከተሞች ከስድሳ ሚልዮን በላይ ሰዎች ባሉበት እንዲቆዩ ተደርገዋል። በዓለም ዙሪያ ለኮረና ቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከ24 ሺህ በላይ ሲደርስ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ያ ቁጥር ከ3 ሺህ በላይ ጨምሯል። በዓለም ዙሪያ ያለውም ሥርጭት ያንኑ ያህል አሳሳቢ ነው። እስካሁን በ25 ሃገሮች ውስጥ ለቫይረሱ መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሰዎች ተገኝተዋል።ለሕልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም በእጅጉ በማሻቀብ ላይ ነው። እጅግ አሳሳቢና አጣዳፊ ሁኔታ ከስቷል።

ተከታዩም ውይይት የወረርሽኙን ዓለም አቀፍ ገጽታ፣ በኢትዮጵያን ያለውን ሁኔታ፣ እንዲሁም ኮረናቫይረስ በተለያየ መልኩ የደቀነውን ፈተና እና ለመከላከል የተያዘውን ዝግጅት ጭምር ይመለከታል።

ተወያዮች በዩናይትድ ስቴትሱ የዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ትምሕርት ፕሮፌሰር እና ከዓለም አቀፍ ጉዞ ጋር የተዛመዱ የሕክምና ጉዳዮች ክትትል ዲሬክተር ናቸው።

“የኮረናቫይረስ ኢትዮጵያ እንዳይገባ” - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:36 0:00
“የኮረናቫይረስ ኢትዮጵያ እንዳይገባ” - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:54 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG