የኮንጎ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔውን የሰጠው ከገዢው ፓርቲ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መሆኑ ተገልጿል።
ወንጀሉን ፈጽመዋል ተብሎ ከተወሰነባቸው የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል። ተከሳሶቹ ወንጀሉን አልፈጸምንም ብለው አስተባብለዋል።
ባራሃርዋ በወቅቱ አንድ የኩዋስ ሜዳ ላይ የተሰበሰቡ ሰዎችን ጦር እየሰበቁ በሉ ለስራ እንንቀሳቀስ ማለትም በውስጠ ታዋቂ አነጋገር ቱትሲዎቹን እንጨፍጭፍ ብለው ሲያነሳሱ ተመልክተናል ብለው እማኞች መስክረውባቸዋል።
ፕረዚደንት ኦባማ እ.አ. አ. በ1945 ዓመት ምህረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በዓለም የመጀመሪያውን አቶሚክ ቦምብ የጣሉባትን ከተማ በመጎብኘት የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስት ፕሬዚደንት ይሆናሉ።
በርምጃው ቁጥራቸው ወደ አራት መቶ ሺህ የሚገመት ስደተኞች ይጎዳሉ ተብሏል። የኬንያ መንግስት ዓርብ ባወጣው መግለጫ ለብሄራዊ ጸጥታችን ስንል ስደተኞን ማስተናገዳችንን ማቆም ይኖርብናል ብለዋል።
የሶሪያ ሰብዓዊ መብቶች የሚከታተለው ቡድን ዛሬ ባወጣው ዘገባ ጂሃዳዊያኑ ቀኑን ሙሉ ከመንግስቱ ሃይሎች ጋር ከተዋጉ በኋላ ዛሬ ማለዳ ካን ቱማን የተባለችውን መንደር እና አካባቢዋን ለመቆጣጠር ችለዋል።
የፍትህና የልማት ፓርቲ የተባለው ገዢ ድርጅት ከፍተኛ ኮሚቴ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንካራ በተደረገ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ ለፓርቲው አንድነት ሲባል የሊቀመንበር ለውጥ ማደረግ ተገቢ ነው ብለዋል።
ተመርጠው በመንግስት ስራ ተሰማርተው የማያውቁት ትራምፕ በምክትል ፕረዚዳንትነት አብሯቸው የሚወዳደር ሰው የፖለቲካ ልምድ ያለው እንዲሆን እንደሚፈልጉ ትላንት ተናግረዋል። ምክትላቸውን በመምረጥ ተግባር የሚረዳቸውን ኮሚቴ እየመሰረቱ ነው።
ፓየስ ማሳይ የተባሉ የመድህን ስራው ሃላፊ ዛሬ ለጋዜጣኞች በተናገሩት መሰረት ዛሬ የተገኘችው ሴት አሁንም ገና ከተቀረቀረችበት ፍርስራሽ ለመውጣት አልቻለችም። ይሁንና ሰራተኞቹ ካስወጥዋት በኋላ ሊያክምዋት ከሚጠባበቁት የህክምና ሰራተኞች ጋር ለመነጋገር ችላለች።
የፍትህ ሚኒስትር አሌክስ ታምብዌ ምዋምባ በርካታ የቀድሞ አሜሪካውያን ወታደሮች በካታንጋ ክፍለ-ሀገር የካቱምቢ ጠባቂዎች ሆነው እንየሰሩ መሆናቸውን የሚያሳይ “የሰነድ መረጃ” አለን ብለዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዙ ሹህ የሚቆጠሩ ሰዎች በተለየዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፈላሽ ሰዎችና የሰራተኞች መብቶች እንዲከበሩ በመጠየቅ ሰልፎች ተካሂደዋል። የጥላቻ መንፈስ የታካለበት የምርጫ ዘመቻ ልፈፋ ያሉትን የተቃወሙ ሰዎችም ታይተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ በቀለ ገርባና በሌሎች ላይ የሽብር ፈጠራ ክሥ ለመመሥረት መወሰኑ በጥልቅ እንዳሳሰበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ።
ውብሸት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዩኒቲ ኮሌጅ ነው የጋዜጠኝነት ሞያውን የጀመረው። ከዚያም አሁን በታገደው ሃዳር በተባለ ነፃ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሞያውን ቀጠለ። እ.አ.አ. ጥር 19, 2012 በአዲስ አበባ የሚገኝ ፍርድ ቤት በአሸባሪነትና እና ለአሸባሪነት ገንዘብ በመከፈል ወንጀለኛ ተባለ።
የሶማልያ (NGO Consortium) ማለትም መንግሥታዊ ያልሆነ የሶማልያ የጋራ መድረክ በመባል የሚታወቀው ይኸው ቡድን ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ባደረገው መግለጫ፤ "የመግብ እጥረቱ፣ በአደገኛነቱ ከሚታወቀው ከኤል-ኒኖ የአየር ንብረት ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል።
ከተገደሉት በተጨማሪ፣ 13 ያህል ሌሎች ወታደሮችም እንደቆሰሉ ተገልጧል።
የኢትዮጵያ ሴት አትሌቶች በማድሪዱ ማራቶን አሸነፉ። አስካለ ዓለማየሁ አንደኛ፥ አበበች ፀጋዬ ሁለተኛ ሆነዋል። የወንዶቹ በኬንያውያኑ የበላይነት ተጠናቀቀ። ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ ጠራርገው ወስደዋል።
የጣምራው ኃይል አዛዥ ይፋ ያደረገው የሟቾቹ ቁጥር በነፃ ምንጭ አልተረጋገጠም። ኦፊሴላዊው የሳዑዲ ዜና አገልግሎት ዛሬ ሰኞ እንዳስታወቀው፣ በጣምራው ኃይል የሚታገዙት የየመን ወታደሮች ጥቃቱን ያካሄዱት፣ የአል-ቃዒዳ ዋና ምሽግ በነበረችው የወደብ ከተማ አል-ሙካላ ውስጥ ነው።
ይህን ይፋ ያደረገው፣ የዓለም ጤና ድርጅት-WHO-የዓለምን የወባ ቀን ሚክናት በማድረግ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ነው።
“የኢትዮጵያ መንግስት ህጻናቱን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ዩኒሴፍም ህጻናቱ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ተለቅቀው ወደቤተሰባቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀርባል” ብሏል።
ችቦውን በርካታ የግሪክ ከተሞችን ለስድስት ቀናት አቋርጦ በሚያልፍበት ወቅት አንድ የዚያችን ሃገር ጥገኝነት የጠየቀውን ሦሪያዊ ስደተኛ ጨምሮ፥ 450 ሰዎች ይቀባበሉታል።
ተጨማሪ ይጫኑ