በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶርያ ውስጥ ከአሌፖ ከተማ አጠገብ በተካሄደ ውጊያ ሰባ ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ

የአሌፖ ከተማንና ከአጠገቧ የምትገኘውን የካን ቱማን መንደር የሚያሳይ ካርታ
የአሌፖ ከተማንና ከአጠገቧ የምትገኘውን የካን ቱማን መንደር የሚያሳይ ካርታ

የሶሪያ ሰብዓዊ መብቶች የሚከታተለው ቡድን ዛሬ ባወጣው ዘገባ ጂሃዳዊያኑ ቀኑን ሙሉ ከመንግስቱ ሃይሎች ጋር ከተዋጉ በኋላ ዛሬ ማለዳ ካን ቱማን የተባለችውን መንደር እና አካባቢዋን ለመቆጣጠር ችለዋል።

ሶርያ ውስጥ የመንግስቱ ሃይሎች እና የአልቃይዳ ግብረ አበር ተዋጊዎች አሌፖ ከተማ አጠገብ ባካሄዱት ውጊያ ሰባ ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ።

አሌፖ ከተማ /ፋይል ፎቶ/
አሌፖ ከተማ /ፋይል ፎቶ/

የሶሪያ ሰብዓዊ መብቶች የሚከታተለው ቡድን ዛሬ ባወጣው ዘገባ ጂሃዳዊያኑ ቀኑን ሙሉ ከመንግስቱ ሃይሎች ጋር ከተዋጉ በኋላ ዛሬ ማለዳ ካን ቱማን የተባለችውን መንደር እና አካባቢዋን ለመቆጣጠር ችለዋል።

መንደርዋ ያለችው ከአሌፖ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲሆን ደማስቆን ከአሌፖ የሚያገናኘው አውራ ጎዳና አቅራቢያ በመሆንዋ ለሽምቅም ተዋጊዎቹ ስትራተጂያዊ ጠቀሜታ ያላት መሆኑ ተጠቁሟል።

ጥቃቱን ያካሄዱት አሌፖ ውስጥ የሚካሄድውን ውጊያ ለማብረድ በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ ባደረጉት ጥረት ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረው ጃኢሽ አል ፋታህ የተባለው ቡድን ተዋጊዎች መሆናቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG