ትናንት ተከብሮ የዋለው "May Day" ወይም የሰራተኞች ቀን በአለም ዙርያ ላሉት ሰርቶ አደሮች ክብር የሚሰጥበት ቀን መሆኑ ይታወቃል። በዚህ አመት ቀኑ እሁድ ላይ ቢውልም የሰራተኞች መብት እንዲከበር የሚሰልፉትን ስዎች ፍላጎት አላሰናከለም።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዙ ሹህ የሚቆጠሩ ሰዎች በተለየዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፈላሽ ሰዎችና የሰራተኞች መብቶች እንዲከበሩ በመጠየቅ ሰልፎች ተካሂደዋል። የጥላቻ መንፈስ የታካለበት የምርጫ ዘመቻ ልፈፋ ያሉትን የተቃወሙ ሰዎችም ታይተዋል።
በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ስያትል ከተማ በመይ ደይ ሰልፍ ላይ የተነሳውን ረብሻ ለመበተን ፖሊሶች የበርበሬ መርጨት ዘዴ ተጠቅመዋል። ዘጠኝ ሰዎች ታስረዋል። አምስት ፖሊሶች በረብሻው እንደተጎዱ ባለስልታኖች ገልጸዋል።
ሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ አንዳንድ ሰልፈኞች የሜክሲኮ ባንዴራንና “ትራምፕን አስወግዱ” የሚሉ መፍክሮች ይዘው ታይተዋል። ለፕረዚዳንትነት በመወዳደር ላይ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚደረገውን ፍልሰት ለማቆም በሜክሲኮና በዩናይትድ ስቴስ መካከል አጥር መስራት እደሚፈልጉ የሚታወቅ ነው።