ዋሽንግተን ዲሲ —
የኦሎምፒክ ችቦ ዘንድሮ ውድድሮቹን ወደ ምታስተናግደው ወደ ሪዮ ዲ ጃኔሮ (Rio De Janero) የብራዚል ከተማ ጉዞ ጀምሯል። ችብው ትናንት አጠር ያላ የማብራት ሥነ ሥርዓት ተደርጎለት ጉዞውን የጀመረው የኦሎምፒክ ውድድሮች ከተጀመሩባት ከግሪክ ከተማ ከኦሎምፒያ (Olympia) ነው።
ችቦውን በርካታ የግሪክ ከተሞችን ለስድስት ቀናት አቋርጦ በሚያልፍበት ወቅት አንድ የዚያችን ሃገር ጥገኝነት የጠየቀውን ሦሪያዊ ስደተኛ ጨምሮ፥ 450 ሰዎች ይቀባበሉታል።
በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ አስተናጋጇ ብራዚል ከገባ በሁዋላም፥ በ 83 ትላልቅና በ 500 አነስተኛ ከተሞቿ ሲያልፍ 12 ሺህ ሰዎች ይቀባበሉታል። የመጨረሻው ሰው በኦሎምፒክ መክፈቻው እለት በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ ችቦውን ማራካና (Maracana) ስታዲየም በተዘጋጀለት ልዩ ሥፍራ ላይ ያኖራል።
በነገራችን ላይ ኦሊምፒክ በአንድ የላቲን አሜሪካ ሃገር ውስጥ ሲዘጋጅ የ 2016ቱ በታሪክ የመጀመሪያው ነው።