በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ-መራሹ ጣምራ ኃይል በየመን ከ800 በላይ የሚሆኑ የአል-ቃዒዳ ተዋጊዎችን እንደገደለ የጦሩ አዛዠ አስታወቀ


የጣምራው ኃይል አዛዥ ይፋ ያደረገው የሟቾቹ ቁጥር በነፃ ምንጭ አልተረጋገጠም። ኦፊሴላዊው የሳዑዲ ዜና አገልግሎት ዛሬ ሰኞ እንዳስታወቀው፣ በጣምራው ኃይል የሚታገዙት የየመን ወታደሮች ጥቃቱን ያካሄዱት፣ የአል-ቃዒዳ ዋና ምሽግ በነበረችው የወደብ ከተማ አል-ሙካላ ውስጥ ነው።

የመን የሚገኘው ሳዑዲ-መራሹ ጣምራ ኃይል ላለፈው አንድ ዓመት በነውጠኞች ይዞታ ስር በሚገኘው ደቡባዊ ከተማ በካሄደ ውጊያ ከ800 በላይ የሚሆኑ የአል-ቃዒዳ ተዋጊዎችን እንደገደለ፣ የጦሩ አዛዠ አስታወቀ።

የጣምራው ኃይል አዛዥ ይፋ ያደረገው የሟቾቹ ቁጥር በነፃ ምንጭ አልተረጋገጠም።

ኦፊሴላዊው የሳዑዲ ዜና አገልግሎት ዛሬ ሰኞ እንዳስታወቀው፣ በጣምራው ኃይል የሚታገዙት የየመን ወታደሮች ጥቃቱን ያካሄዱት፣ የአል-ቃዒዳ ዋና ምሽግ በነበረችው የወደብ ከተማ አል-ሙካላ ውስጥ ነው።

ወታደራዊ ምንጮች ለፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃል፣ የጣምራው ኃይል ወደከተማዪቱ ሲገባ፣ ወደ ምዕራቡ ክፍል ካፈገፈጉት ከአል-ቃዒዳ ታጣቂዎች ምንም ዓይነት መቋቋም አልደረሰበትም ብለዋል።

በውጊያው ወቅት በርካታ የአል-ቃዒዳ አዛዦች ተገድለዋል፤ በሲቪሎች ሕይወት ላይ ስለደረሰ ሞት ግን የተገለጸ ነገር የለም።

XS
SM
MD
LG