በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወባ ክፉኛ የሚያጠቃቸው 6 የአፍሪቃ አገሮች እ.አ.አ. በ2020 ከህመሙ ነፃ እንደሚሆኑ ተገለጸ


ይህን ይፋ ያደረገው፣ የዓለም ጤና ድርጅት-WHO-የዓለምን የወባ ቀን ሚክናት በማድረግ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ነው።

በቀጣዮቹ 4 ዓመታት ውስጥ፣ እ.አ.አ. በ2020 መሆኑ ነው፣ ወባ ክፉኛ የሚያጠቃቸው 6 የአፍሪቃ አገሮች ከህመሙ ነፃ እንደሚሆኑ ተገለጸ።

ይህን ይፋ ያደረገው፣ የዓለም ጤና ድርጅት-WHO-የዓለምን የወባ ቀን ሚክናት በማድረግ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ነው።

ባለፈው ዓመት በWHO የጸደቀውና ወባን ከ2016-2020 ለማጥፋት ተብሎ በተነደፈው ዓለማቀፍ ቴክኒካዊ ስልት መሠረት፣ በጠቅላላው እ.አ.አ. በ2020 10 አገሮች ከወባ ነፃ ሲሆኑ፣ ስድስቱ ከአፍሪቃ ናቸው። እ.አ.አ. ከ2000 ዓ.ም. ወዲህ በወባ ህመም የሚደርሰው ሞት ከዓለማችን በ60% እንደቀነሰ ተመልክቷል።

አፍሪቃ ውስጥ በ2020 ከወባ ነፃ የሚሆኑት ስድስቱ አገሮች አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕ-ቨርዴ፣ ኰሞሮስ፣ ደቡብ አፍሪቃና ስዋዚላንድ ናቸው።

XS
SM
MD
LG