በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ አደጋ የ6 ወር ህጻን ልጅ ዳነች ዛሬም አንዲት ሴት በህይወት ተገኝታለች


ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ አደጋ የስድስት ወር ህጻን ዴለሪን ሳሲ ዋሲኬ በፍርስራሹ ስር በህይወት ድናለች። ኬንያ በሚገኘው ኬንያታ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት ትገኛለች።
ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ አደጋ የስድስት ወር ህጻን ዴለሪን ሳሲ ዋሲኬ በፍርስራሹ ስር በህይወት ድናለች። ኬንያ በሚገኘው ኬንያታ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት ትገኛለች።

​​ፓየስ ማሳይ የተባሉ የመድህን ስራው ሃላፊ ዛሬ ለጋዜጣኞች በተናገሩት መሰረት ዛሬ የተገኘችው ሴት አሁንም ገና ከተቀረቀረችበት ፍርስራሽ ለመውጣት አልቻለችም። ይሁንና ሰራተኞቹ ካስወጥዋት በኋላ ሊያክምዋት ከሚጠባበቁት የህክምና ሰራተኞች ጋር ለመነጋገር ችላለች።

የናይሮቢ ኬንያ የመድህን ሰራተኞች ለአንድ ሳምንት ከሚጠጋ ጊዜ በፊት ከተደረመሰው የአፓርትማ ህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የ6 ወር ህጻን ልጅ ማክሰኞ ሲያድኑ ዛሬ ደግሞ አንዲት ሴት በህይወት አገኙ። ህንጻው ሲደረመስ ቢያንስ 26 ሰዎች ሞተዋል።

የስድስት ወር ህጻን ዴለሪን ሳሲ ዋሲኬ አባት ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጠ
የስድስት ወር ህጻን ዴለሪን ሳሲ ዋሲኬ አባት ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጠ

ፓየስ ማሳይ የተባሉ የመድህን ስራው ሃላፊ ዛሬ ለጋዜጣኞች በተናገሩት መሰረት የተገኘችው ሴት አሁንም ገና ከተቀረቀረችበት ፍርስራሽ ለመውጣት አልቻለችም። ይሁንና ሰራተኞቹ ካስወጥዋት በኋላ ሊያክምዋት ከሚጠባበቁት የህክምና ሰራተኞች ጋር ለመነጋገር ችላለች።

“ለመንቀሳቀስ አትችልም። ግን ደህነ ናት” ሲሉ ሃላፊው ለሮይተርስ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ባለፈው ማክሰኞም የኬንያ የቀይ መቀል ድርጅት አንድ ህጻን ልጅን ከተቀረቀረችበት ለማውጣት ችሏል። ህጻኗ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው በፍርስራሹ ስር የተገኘችው።

135 የሚሆኑ ሰዎችን ከአደጋው ለማትረፍ ተችሏል። በርካታ ሌሎች ሰዎች ገና የገቡበት አልታወቀም። ባለስልታኖች ከአሁን ወዲህ በፍርስራሹ ውስጥ በህወት ያለ ሰው እናገኛለን የሚል እምነት እንደሌላቸው አስገንዝበዋል።

ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ 12 ሲሞቱ ሎሎች በፍርስራሹ ስር እንዳሉ ተሰግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:34 0:00

XS
SM
MD
LG