ዋሽንግተን ዲሲ —
የኬንያ አትሌቶች በለንደን ማራቶንም ቀንቷቸዋል። በሁለቱም ፆታዎች ነው ያሸነፉት። በተለይ የሴቶቹን ጀሚማ ሱምጎንግ (Jemima Sumgong) ውኃ ማደያው ሥፍራ ላይ ከኢትዮጵያዊቷ አሰለፈች መርጊያ ጋር ተጋጭታ ከወደቀች በኋላ ተነስታ ማሸነፏ፥ ብዙዎችን አስደንቋል።
በወንዶቹ ኢሉድ ኪፕቾጌ (Eluid Kipchoge) ሻምፒየንነቱን ተከላክሏል። በሌላ ያትሌቲክስ ስፖርት ዜና፥ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የሰነበተውን 45ኛ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር መከላከያ አሸንፏል።
በቱር ኤርትራ (Tour Eritrea) ቢሲክሌት ውድድር የኤርትራ ጋላቢዎች በአንደኝነት አጠናቀዋል።