በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ የጃፓኑዋን ሂሮሺማ ከተማ ይጎበኛሉ

የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ሂሮሺማንና ሊላዋን በሶስተኛው ቀን ቦምብ የተጣለባትን ናጋሳኪን ከ1945 እስካሁን አልጎበኙም /ፋይል ፎቶ-የሂሮሺማ መታሰብያ/
የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ሂሮሺማንና ሊላዋን በሶስተኛው ቀን ቦምብ የተጣለባትን ናጋሳኪን ከ1945 እስካሁን አልጎበኙም /ፋይል ፎቶ-የሂሮሺማ መታሰብያ/

ፕረዚደንት ኦባማ እ.አ. አ. በ1945 ዓመት ምህረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በዓለም የመጀመሪያውን አቶሚክ ቦምብ የጣሉባትን ከተማ በመጎብኘት የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስት ፕሬዚደንት ይሆናሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ የጃፓኑዋን ሂሮሺማ ከተማ ይጎበኛሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ የጃፓኑዋን ሂሮሺማ ከተማ ይጎበኛሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:05 0:00

ፕረዚደንት ኦባማ እ.አ. አ. በ1945 ዓመት ምህረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በዓለም የመጀመሪያውን አቶሚክ ቦምብ የጣሉባትን ከተማ በመጎብኘት የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስት ፕሬዚደንት ይሆናሉ።

የጃፓን ሂሮሺማ ካርታ
የጃፓን ሂሮሺማ ካርታ

ላለፉት ሰባ ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ሂሮሺማንና ሊላዋን በሶተኛው ቀን ቦምብ የተጣለባትን ናጋሳኪን ከመጎብኘት ተቆጥበው ቆይተዋል። የዚህም ምክንያት የጎበኘን እንደሆን የቦምብ ጥቃቶቹ ላደረሱት ውድመት ይቅርታ የጠየቅን ያስመስልብናል በሚል ነው።

ዋይት ሃውስ እንዳስታወቀው ፕሬዚደንት ኦባማ እ.አ.አ. ከመጪው ግንቦት ሃያ አንድ እስከ ሃያ ስምንት በቪየትናምና ጃፓን በሚያደርጉት ጉብኝት ማጠናቀቂያ ላይ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ሆነው ሂሮሺማን ይጎበኛሉ።

ፕሬዚድንቱ በሂሮሺማና ናጋሳኪ ላይ ስለተፈጸሙት የኣቶሚክ ቦምብ ጥቃቶች ይቅርታ ሊጠይቁ አለመሆኑን ግን አማካሪያቸው ቤን ሮድስ አረጋግጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ውች ጉዳይ ሚንስትር በሂሮሺማ መታሰብያ ላይ አበባ እያሰፈሩ /ፋይል ፎቶ/
የዩናይትድ ስቴትስ ውች ጉዳይ ሚንስትር በሂሮሺማ መታሰብያ ላይ አበባ እያሰፈሩ /ፋይል ፎቶ/

ፕሬዚደንቱ የሚሄዱት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ የአቶሚክ ቦምብ ለመጠቀም የተደረገውን ውሳኔ ተመልሰው ለመገምገም ሳይሆን ይልቁንም ከጃፓን ጋር በጋራ የሚኖረንን የወደፊት ዕጣ በተመለከተ ራዕያቸውን የሚያካፍሉበት ጉብኝት ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG