ዋሽንግተን ዲሲ —
ሶማልያ፣ በድርቅና በመግብ እጥረት ምክኒያት፣ እ.አ.አ. በ2010 ዓ.ም. እንደነበረው ላለ ረሀብ የመጋለጥ አደጋ ላይ መሆኗን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ 23 ድርጅቶች የሚገኙበት ቡድን አስታወቀ።
የሶማልያ (NGO Consortium) ማለትም መንግሥታዊ ያልሆነ የሶማልያ የጋራ መድረክ በመባል የሚታወቀው ይኸው ቡድን ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ባደረገው መግለጫ፤ "የመግብ እጥረቱ፣ በአደገኛነቱ ከሚታወቀው ከኤል-ኒኖ የአየር ንብረት ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል።
ኤል-ኒኞ፣ በአፍሪቃ ቀንድ አገሮች ላይ ከፍተኛ የአይር መዛባትና ብሎም ድርቅ ማስከተሉ ይታወቃል።
መንግሥታዊ ያልሆነው የሶማልያው ኮንሶርቲየም ይፋ ያደረገው መግለጫ፣ ጄኔቫ ላይ ከኤል-ኒኞ ጋር በተያያዘ ከሚካሄደው የሰብዓዊ እርዳታ ስብሰባ ጋር እንዲገጣጠም ተደርጎ የወጣ መሆኑም ታውቋል።