በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደዋ ውስጥ ከአል-ሸባብ ጋር በተካሄደ ውጊያ 8 የመንግሥት ወታደሮች እንደተገደሉ ባለሥልጣናት አስታወቁ


ከተገደሉት በተጨማሪ፣ 13 ያህል ሌሎች ወታደሮችም እንደቆሰሉ ተገልጧል።

ሶማልያ ውስጥ የሚገኙ የአል-ሸባብ ነውጠኞች፣ ባይደዋ (Baidoa)ከተማ አቅርቢያ በተካሄደ ውጊያ፣ ቢያንስ 8 የመንግሥት ወታደሮችን እንደተገደሉ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

አንድ የሶማልያ ጦር አዛዥ ለቪኦኤ ሶማልኛ አልግሎት በሰጡት ቃል፣ በአንድ ወታደታዊ ጦር ሰፈር የሚገኙ የመንግሥቱን ወታደሮች ለማጠናከር በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ኃይል ይዞ በሚጓዘው ኮንቮይ ላይ፣ ነውጠኞቹ በከፈቱት ተኩስ ነው ጥቃቱ የደረሰውና ስምንቱ ወታደሮች የተገደሉት ብለዋል።

ከተገደሉት በተጨማሪ፣ 13 ያህል ሌሎች ወታደሮችም እንደቆሰሉ ተገልጧል።

የአል-ሸባብ ታጣቂ
የአል-ሸባብ ታጣቂ

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ትናንት ሰኞ ከሞቅዲሾ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ፣ ሶማልያ ውስጥ ባሉ የአፍሪቃ ሕብረት ወታደሮች ላይ ጥቃት ያካሄድኩት እኔ ነኝ ሲል፣ ነውጠን/ኛው ISIS ኃላፊነቱን ወሰደ።

በአይስስ (ISIS) በድረ-ገጹ ባሰፈረው መረጃ፣ ትሬዲቺ Tredici በተሰኘች መንደር ውስጥ የተከልንው ፈንጂ፣ የአሚሶም (AMISOM) ወታደሮች የነበሩባትን ተሸርካሪ ማውደም ችሏል ብሏል።

አስተያየቶችን ይዩ (2)

XS
SM
MD
LG