በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይስስን ለመርዳት አሲረዋል ለተባሉ ሶስት ሶማሊያዊ-አሜሪካዊያን የፍርድ ሸንጎ መረጣ ተጀምሯል


ከሚንሶታ ፖሊስ/ሸሪፍ ጣብያ የተገኘ የሃያ ሁለት ዓመቱ ሞሃመድ ፋራህ ፎቶ
ከሚንሶታ ፖሊስ/ሸሪፍ ጣብያ የተገኘ የሃያ ሁለት ዓመቱ ሞሃመድ ፋራህ ፎቶ

ወንጀሉን ፈጽመዋል ተብሎ ከተወሰነባቸው የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል። ተከሳሶቹ ወንጀሉን አልፈጸምንም ብለው አስተባብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሚኔሶታ ክፍለ ሃገር ውስጥ የእስልምና መንግስት ብሎ ራሱን የሚጠራውን ቡድን ለመርዳት አሲረዋል ተብለው የተከሰሱ ሶስት ሶማሊያዊ-አሜሪካዊያን የፍርድ ሂደት ከህዝብ የተውጣጡ የፍርድ ሸንጎ መረጣ ተጀምሯል።

የሃያ ሁለት ዓመቱ ሞሃመድ ፋራህ፣ የሃያ አንድ ዓመቱ ጉሌድ ኦማር፣ እና የሀያ ሁለት ዓመቱ አብዲራሂማን ዳኡድ ጽንፈኛውን ቡድን ለመቀላቀል ወደ ሶሪያ ለመጓዝ ከሁሉም የሚያዋጣው መንገድ የቱ እንደሆነ ባለፉት መጋቢት እና ሚያዝያ ወራት በተደጋጋሚ እየተገናኙ ከተመካከሩ በርካታ የሚኔሶታ ነዋሪዎች ሶስቱ መሆናቸው ተነግሯል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል አቃቤ ህግ ሶስቱ ሰዎች ወደ ውጭ ሃገር ተጉዘው ግድያ ሊፈጽሙ አሲረዋል ብሎ ወንጅሏቸዋል። ወንጀሉን ፈጽመዋል ተብሎ ከተወሰነባቸው የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል። ተከሳሶቹ ወንጀሉን አልፈጸምንም ብለው አስተባብለዋል።

XS
SM
MD
LG