በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ትራምፕ በአጠቃላዩ ምርጫ በምክትል ፕረዚዳንትነት አብረዋቸው የሚወዳደር ሰው መፈለግ ጀምረዋል

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለፕረዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሪፑብሊካዊ ዶናልድ ትራምፕ
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለፕረዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሪፑብሊካዊ ዶናልድ ትራምፕ

ተመርጠው በመንግስት ስራ ተሰማርተው የማያውቁት ትራምፕ በምክትል ፕረዚዳንትነት አብሯቸው የሚወዳደር ሰው የፖለቲካ ልምድ ያለው እንዲሆን እንደሚፈልጉ ትላንት ተናግረዋል። ምክትላቸውን በመምረጥ ተግባር የሚረዳቸውን ኮሚቴ እየመሰረቱ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለፕረዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሪፑብሊካዊ ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ውክልና እንደሚያገኙ በተረጋገጠበት በአሁኑ ወቅት በአጠቃላዩ ምርጫ በምክትል ፕረዚዳንትነት አብረዋቸው የሚወዳደር ሰው መፈለግ ጀምረዋል።

ተመርጠው በመንግስት ስራ ተሰማርተው የማያውቁት ትራምፕ በምክትል ፕረዚዳንትነት አብሯቸው የሚወዳደር ሰው የፖለቲካ ልምድ ያለው እንዲሆን እንደሚፈልጉ ትላንት ተናግረዋል። ምክትላቸውን በመምረጥ ተግባር የሚረዳቸውን ኮሚቴ እየመሰረቱ ነው።

ትራምፕ በመጪው ህዳር ወር በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ከሂለሪ ክሊንተን ጋር ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ይታመናል።

ይሁንና ክሊንተን የዲሞክራስያዊው ፓርቲ ውክልናን ገና አልጨበጡም።

ተወዳዳርያቸው የቨርሞንት ክፍለ-ሀገር ሴኔተር በርኒ ሳንደርስ በ ሲ ቢ ኤስ (CBS) የአሜሪካ ቴሌቪዥን ጣብያ ሲናገሩ የተቀዳሚው ምርጫ በመጪው ሰኔ ወር ከማብቃቱ በፊት ውድድሩን የማቆም እቅድ የለኝም ብለዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG