በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩኒሴፍ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የጋምቤላ ህጻናትን ጠልፈው መውሰዳቸውን አጥብቆ አወገዘ


ከደቡብ ሱዳን የተሰደደ ህጻን በጋምቤላ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ [ፋይል - ፎቶ ሮይተርስ]
ከደቡብ ሱዳን የተሰደደ ህጻን በጋምቤላ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ [ፋይል - ፎቶ ሮይተርስ]

“የኢትዮጵያ መንግስት ህጻናቱን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ዩኒሴፍም ህጻናቱ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ተለቅቀው ወደቤተሰባቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀርባል” ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ (UNICEF) የኢትዮጵያውያኑን ህጻናት መጠለፍ አውግዞታል።

ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ የደቡብ ሱዳን የከብት ዘራፊዎች ናቸው የተባሉ የታጠቁ አጥቂዎች ባደረሱት ዘግናኝ ጥቃት አንድ መቶ የሚሆኑ ህጻናትን ማገታቸውን እጅግ አጥብቀን እናወግዛለን ብሏል። ሁኔታውን እየተከታታተለ መሆኑንና ለታጠቂዎቹ ማኅበረሰቦች ርዳታ ለማድረግ ዝግጁነቱን ገልጿል። በምንም ምክንያት በህጻናት ላይ የሚፈጸም ጥቃት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን በጋራ ስብዕና ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው ሲል ዩኒሴፍ ኮንኗል።

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት አርማ
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት አርማ

“የኢትዮጵያ መንግስት ህጻናቱን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ዩኒሴፍም ህጻናቱ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ተለቅቀው ወደቤተሰባቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀርባል” ብሏል።

በሌላ በኩል የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ባሽር ጋባንዲ (Bashir Gbandi) የኢትዮጵያ ወታደሮች በጋምቤላ ጥቃት ያደርሱትን ደቡብ ሱዳናውያን እያሳደዱ ነው?

የኢትዮጵያ ወታደሮች ደቡብ ሱዳን ግዛት ገብተው ኣጥቂዎቹን እንዲያድኑ የጁባ መንግስት ፈቃድ ሰጥቱዋል? በርግጥስ ገብተዋል? ተብለው ጁባ ውስጥ በተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ በየአሜሪካ ድምጽ የደቡብ ሱዳን አገልግሎት ዘጋቢ ተጠይቀው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የጸጥታ ጉዳይ በመሆኑ ለጋዜጠኛ ልናገር አልችልም ያሉት ምክትል ሚኒስትሩ ሆኖም መንግስታቸው ከኢትዮጳያ መንግስት ጋር ኣብሮ ጉዳዩን እየተከታተለ ነው ብለዋል። የኤስ ፒ ኤል ኤ (SPLA) ጠቅላይ የጦር ኣዛዥ ጄነራል ፖል ማሎንግ (Paul Malong) በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር በመጪዎቹ ቀናት ወደአዲስ አበባ እንደሚጉዋዙ የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG