በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት የቀድሞ የሩዋንዳ ከንቲባዎች በሀገሪቱ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት በተያያዘ ፈረንሳይ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበዋል

የዘር ማጥፋትን የሚዋጉ የመብት ተሟጋች አልየን ጋውቲየር እና ባለቤታቸው ዳፍሮዛ ጋውቲየር በፓሪስ ፍርድ ቤት /ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/
የዘር ማጥፋትን የሚዋጉ የመብት ተሟጋች አልየን ጋውቲየር እና ባለቤታቸው ዳፍሮዛ ጋውቲየር በፓሪስ ፍርድ ቤት /ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/

ባራሃርዋ በወቅቱ አንድ የኩዋስ ሜዳ ላይ የተሰበሰቡ ሰዎችን ጦር እየሰበቁ በሉ ለስራ እንንቀሳቀስ ማለትም በውስጠ ታዋቂ አነጋገር ቱትሲዎቹን እንጨፍጭፍ ብለው ሲያነሳሱ ተመልክተናል ብለው እማኞች መስክረውባቸዋል።

ሁለት የቀድሞ የሩዋንዳ ከንቲባዎች በሀገሪቱ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት እና በስብዕና ላይ ወንጀል መፈጸም በተያያዘ ትናንት ፈረንሳይ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የስድሳ ስምንት ዓመቱ ቲቴ ባራሂርዋ እና የሃምሳ ስምንት ዓመቱ ኦክቲቪየን ንጌንዚ እ. አ. አ. ሚያዝያ አስራ ሶስት 1994 ዓመተ ምህረት በምስራቅ ሩዋንዳዋ ካባሮንዶ ከተማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ከዘር ፍጅት ለማምለጥ የተደበቁ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ በቀጥታ ሚና ተጫውተዋል ተብለው ተከሰዋል።

ባራሃርዋ በወቅቱ አንድ የኩዋስ ሜዳ ላይ የተሰበሰቡ ሰዎችን ጦር እየሰበቁ በሉ ለስራ እንንቀሳቀስ ማለትም በውስጠ ታዋቂ አነጋገር ቱትሲዎቹን እንጨፍጭፍ ብለው ሲያነሳሱ ተመልክተናል ብለው እማኞች መስክረውባቸዋል።

ሁለቱም የቀድሞ ከንቲባዎች ክሱን አስተባብለዋል። ጥፋተኞች ሆነው ከተበየነባቸው የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።

የፍርድ ሂደቱ ስምንት ሳምንታት እንደሚፈጅ ሲጠበቅ የሚበዙት ከሩዋንዳ የተጉዋዙ የሆኑ ከመቶ የሚበልጡ የጥቃቱ ሰለባዎች፡ የሰለባዎች ዘመዶች ኣና ምስክሮች ፓሪስ ፍርድ ቤት የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ ። ፈረንሳይ ከሩዋንዳው የዘር ፍጅት በተያያዙ ወንጀሎች የተከሰሱ ሰዎችን እንድትዳኝ ከተባባሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ፈቃድ ኣግኝታለች

XS
SM
MD
LG