ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ - ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወም ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ አካሄዱ። ሰልፈኞቹ ተቃውሞውን ያደረጉት መንግሥት በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ይደርሳል ያሉትን የመብት ረገጣዎች ለማጋለጥ እንደሆነ ገልፀዋል።
ከተያዙበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ ክፍል የማምለጥ ሙከራ አላደረግኩም ሲሉ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ) ዛሬ ለችሎት ተናግረዋል። ባለፈው ሐምሌ መጨረሻ ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂግጂጋ ውስጥ ተነስቶ ከነበረው ሁከትና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ተይዘው እሥር ላይ የሚገኙት አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ) ያረፉበትን በር መስተዋት ሰብረው ለማምለጥ ሞክረዋል ሲል ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል።
በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ለማንሳት በዚያች ሃገር ተጨባጭ ለውጦች መካሄድ ይኖርባቸዋል ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት አስገንዝበዋል።
በምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ሃገር እየተካሄዱ ያሉ ከዚህ ቀደም ታይተው ያልታወቁ ለውጦችን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር ያሏትን ግንኙነቶች ማጠናከር አለባት ሲሉ አንድ ከፍተኛ አሜሪካዊ ዲፕሎማት አስገነዘቡ።
በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ኮንግሬስ ማን ክሪስ ስሚዝ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቆይታ
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጅቡቲ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ባደርጉት ሰፊ ውይይት፤ ጅቡቲና ኤርትራ ከዚህ ቀደም የነበራቸው ችግር በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት መስማማታቸውን የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
አምስት አባላት ያሉት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ቡድን የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለመከታተልና በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና እና በዴሞክራሲ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ለማድረግ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ያመራል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ኤችአር 128 በሚል መጠርያ ሰብአዊ መብት እንዲከበርና አካታች አስተዳደር እንዲኖር የሚጠይቀውን ደንብ ከሚያራምዱት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት አንዱ የኮሎራዶ ተወካይ ማይክ ኮፍማን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የፖለቲኣ እስረኞችን በመፍታታቸውና ከኤርትራ ጋር የሰላም ሥምምነት በማድረጋቸው አሞግሰዋቸዋል።
ትናንት በምሥራቅ ሃረርጌ ቆርኬ በተባለ የሃሮማያ ቀበሌ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች እንደሞቱና 36 እንደቀሰሉ ተነገረ፡፡
ኦሮምያ ውስጥ አልፎ አልፎ ይታያል ያሉትን የሥርዓተ-አልበኝነት ችግር ለማስወገድ ከሕዝብ ጋር ሆነው እንደሚሠሩ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮምያና ሶማሌ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ላይ ሲነሱ በቆዩ ግጭቶች ምክንያት ኦሮምያ ውስጥ 159 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የአሥረኛና የአሥራ ሁለተኛ ክፍሎች ተማሪዎች ፈተና በሚወስዱበት ጊዜ በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች አዋሣኝ አካባቢዎች ውስጥ “የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ያደርሰዋል” በሚባል ጥቃት ምክንያት ብዙ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውንና የብዙ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ሂደት መስተጓጎሉን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየጊዜው ደረሱብን በሚሉ የፌደራልና የመከላከያ ጥቃቶች ሳቢያ ትምህርታቸውን ካቋረጡ ከአንድ ወር በላይ እንደሆናቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
በምሥራቅ ሀረርጌ ዞን ጉሚ ቦርደዴ ወረዳ ኦቦንሳ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ከሶማሌ ክልል የመጣው ልዩ ኃይል ዛሬ ጠዋት በደረሰው ጥቃት የ6 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎችና የወረዳ ባለሥልጣናት ገልፀዋል፡፡
በኦሮምያ ክልል የቦረና ዞን ሦስት የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች በትላንት እና በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄዳቸው ተዘገበ።
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን በሊባን ወረዳ ጥቃት አድርሰው ሰባት ሰዎችን ገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ የኦሮምኛ ዝግጅት ክፍል ገልፀዋል።
ከሶማሌ ክልል ጋር አዋሣኝ በሆኑ የተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ውስጥ ሰሞኑን እየታዩ ያሉ ጥቃቶችና ግጭቶች ተዛምተው ዛሬ ባሌ ውስጥ ራይቱ ወረዳ ላይ ቁጥሩ ከአሥር በላይ ሰው መገደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል።
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከሶማሌ ክልል የመጡ የልዩ ፖሊስ አባላት በሞያሌ ወረዳ ጫሙቅ እና ጎፋ በተባሉ ስፍራዎች ላይ ትናንት ጠዋት ጥቃት ከፍተው ከአሥር በላይ ሰዎች ገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ሀገር ውስጥ በስደት ላይ ያሉ ብዙ መቶ ሺህዎች ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት ያለውን ዕቅድ እንዲገታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት /ሂዩማን ራይትስ ዋች/ አሳሰበ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በሱማልያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ የመንና ናይጄሪያ በተከሰተው ድርቅና በአካባቢዎቹ እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ምክንያት ለረሃብ የተጋለጡ ሕዝቦችን ለመመገብ የ639 ሚሊዮን አሜሪካ ዶላር ለመርዳት ቃል ገብተዋል።
በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች የተቀሰቀሰው ግጭት መቀጠሉንና በዚህም በሁለት ቀናት ውስጥ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በደቡብ ኦሮሚያ በነገሌ ቦረና አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ገለጹ። የጉጂ ዞን የፀጥታ ኃላፊ ችግሩን በመንግሥትና በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ