ዋሺንግተን ዲሲ —
በቦረና ዞን የሞያሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አስቻለው ዮሃንስ “የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል” እያደረሰ ነው ባሉት ተከታታይ ጥቃት ምክንያት በዚህ ዓመት ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎች የትምህርት ዕድል መጨናገፉን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከተማዪቱ “የግጭቶች ሥፍራ እንድትሆን ሁኔታዎች በማስገደዳቸው መሠረታዊ ልማትም ተስተጓጉሎባታል” ብለዋል ከንቲባው።
ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ላይ ቦምብ እንደሚጣል፣ መሣሪያ እንደሚተኮስ የገለፁት አቶ አስቻለው ቤተሰቦችና ተማሪዎችም ከተማዪቱ ውስጥ በነፃነት መንቀሳቀስ መቸገራቸውን አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ያነጋገራቸው የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ባጋጃ ሞርጌ በግጭቶቹ ምክንያት በወረዳው ውስጥ ስድስት የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ