በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች በኦሮምያ ጉዳት ማድረሳቸው ተነገረ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

ከሶማሌ ክልል ጋር አዋሣኝ በሆኑ የተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ውስጥ ሰሞኑን እየታዩ ያሉ ጥቃቶችና ግጭቶች ተዛምተው ዛሬ ባሌ ውስጥ ራይቱ ወረዳ ላይ ቁጥሩ ከአሥር በላይ ሰው መገደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል።

ከሶማሌ ክልል ጋር አዋሣኝ በሆኑ የተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ውስጥ ሰሞኑን እየታዩ ያሉ ጥቃቶችና ግጭቶች ተዛምተው ዛሬ ባሌ ውስጥ ራይቱ ወረዳ ላይ ቁጥሩ ከአሥር በላይ ሰው መገደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል።

በሞያሌ ወረዳ ጫሙቅ ቀበሌ አቅራቢያ ትናንት ለብዙ ሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ጥቃት ዛሬም በጎፋ ቀበሌ መቀጠሉ ተሰምቷል።

ተመሣሣይ ግጭት በጉጂ ዞን በነገሌ ቦረና አካባቢም ዛሬ መዛመቱን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ከሶማሌ ክልል የተነሱ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ባሌ ራይቱ ወረዳ መግባታቸውን ለቪኦኤ ያረጋገጡት የኦሮምያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ የደረሰውን ጉዳት ስፋት ለጊዜው በውል እንደማያውቁ ተናግረዋል።

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉዳዩን ያውቅ እንደሆነና የሚሰጠውም ምላሽ እንዳለ ለመጠየቅ ወደ ክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ወደ ክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ፤ በተጨማሪም ወደ ፌደራል ጉዳዮች የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በበርካታ ቁጥሮች ያደረግናቸው ጥሪዎች ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች በኦሮምያ ጉዳት ማድረሳቸው ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:31 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG