ሶማሌ ክልል የመጡ የልዩ ፖሊስ ኃይሎች በቦረናና በጉጂ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ገብተው ባለፉት አራት ቀናት ውስጥ የአምስት ሰዎችን ሕይወት ማጥፋታቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ኦሮምያ ክልል ጂማ ዞን የሊሙ ሴቃ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ብዙ ሰዎች እየታሠሩ መሆኑንና የሚያዙትም እጅግ ጠባብ በሆነ ክፍል ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኔጌሌ ቦረና ከተማና በገጠር መንደሮች ከ2መቶ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከስራ ገበታቸው ላይ ተይዘው ሲታሰሩ ከቤተስቦቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ምንጮች ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱትን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተከትሎ ከታየው የጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ ወደ የሚማሩባቸው ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች መሄድ ተስተጓጉለው ከሰነበቱት ተማሪዎች፤ የተወሰኑት ትምህርት መጀመራቸው እየተነገረ ነው።
በኒውዮርክ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ረፋዱ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ደጃፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙ በኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት የተዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በዋይት ሃውስ ፊት ለፊትና በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በር ተካሄዷል።
ሂላሪ ክሊንተን የዴሞክራቲክ ፓርቲያቸው እጩ ሆነው ተመረጡ። በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የአንድ አብይ ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ በመሆንም ታሪክ ሠሩ።
“ከዚህ ቀደም ማንም! ወንድም ሆነ ሴት፤ እኔ አይደለሁም! ቢል አይደለም! ማንም! ይህችን አገር ለመምራት የሂላሪን ያህል ብቃት ኖሮት አያውቅም!” የዩናይትድ ስቴሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ “ተተኪዬ” ስላሏቸው ሴናተር ሂላሪ ክሊንተን የተናገሩት።
“እንደምን ዋላችሁ ልዑካን! አንዳች ታሪክ እውን ልናደርግ ተዘጋጅተናል?” የኦሃዮ ክፍለ ግዛቷ ዲሞክራት ማርሻ ፈጅ፤ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ልዑካን ሂላሪ ክሊንተንን የፓርቲው እጩው ያደረጉበትን ድምጽ ለመስጠት በተሰናዱበት ያቀረቡት ሃሳብ አዘል ጥያቄያቸው።
በደቡብ ኦሮምያ፤ ቦረና ዞን ውስጥ ትናንት፣ ዓርብ ምሽት ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ የ13 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ወራት በኦሮምያ ክልል እየታየ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ዛሬ በአሜሪካ ኮንግረስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የቢሾፍቱ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ትናንትና እና ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸውንና በፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎችና ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
አራት ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሚያ ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደቀጠለ መኾኑን ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው። ከትናንት ወድያ ማምሻውን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በነበረ ተቃዎሞ ተማሪዎች መታሠራቸው ተነሯል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የታሠረ ተማሪ የለም ብለዋል።
ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ የሚያካሂደውን ግድያ ያቁም፣ ኦሕዴድ ሥልጣን ይልቀቅ፣ ለተጎዱ ካሣ ይከፈል የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን የያዙ ነበሩ።
አራተኛ ወሩን የያዘው በኦሮሚያ የተለያዩ የዞን ከተሞች እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ የቀጠለ ሲኾን በያቤሎ፣ በአሬሮ፣ ሂድ ሎላ፣ በጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተሞች የተደረጉ ሰልፎች አብዛኞቹ ሕገወጥ ናቸው። በአንዳንዶቹ ቦታዎች ደግሞ ከሕዝቡ ጋር እየተነጋገርን ነው ሲል የወረዳ እና የዞኑ ባለሥልጣናት ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡
የኦሮሚያ ተቃውሞ ዛሬም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ መዋሉ ተነግሯል። አንዳንድ ባለሥልጣናት ግን የቆሰለም ሆነ የሞተም የለም ብለዋል።
በአምቦ እስር ቤት ተቃጥሏል፤አንድ የዘጠኝ ዓመት አዳጊ ተገድሏል
ኒው ዮርከ ከተማ ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ፅ/ቤት ደጅ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ እየፈፀመ ናቸው ያሏቸውን አድራጎቶች በመቃወም ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች የተጠራሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ አድርገዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ