በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች ግጭት 18 ሰው መሞቱ ተገለፀ

(ፎቶ ፋይል፡ ከሰሜን የኬንያ አቅራቢያ እአአ በሐምሌ 11/2008 ዓ.ም የተነሰ አጠቃላይ የሞያሌን አካባቢ ስዕል የሚሰጥና የደቡብ ኦሮሚያና የሶማሌ ክልልን አዋሳኝ ቦታዎች የሚያሳይ ፎቶ ነው። ፎይተርስ)
(ፎቶ ፋይል፡ ከሰሜን የኬንያ አቅራቢያ እአአ በሐምሌ 11/2008 ዓ.ም የተነሰ አጠቃላይ የሞያሌን አካባቢ ስዕል የሚሰጥና የደቡብ ኦሮሚያና የሶማሌ ክልልን አዋሳኝ ቦታዎች የሚያሳይ ፎቶ ነው። ፎይተርስ)

በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች የተቀሰቀሰው ግጭት መቀጠሉንና በዚህም በሁለት ቀናት ውስጥ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በደቡብ ኦሮሚያ በነገሌ ቦረና አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ገለጹ። የጉጂ ዞን የፀጥታ ኃላፊ ችግሩን በመንግሥትና በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች የተቀሰቀሰው ግጭት መቀጠሉንና በዚህም በሁለት ቀናት ውስጥ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በደቡብ ኦሮሚያ በነገሌ ቦረና አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ገለጹ። የጉጂ ዞን የፀጥታ ኃላፊ ችግሩን በመንግሥትና በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች ግጭት 18 ሰው መሞቱ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:55 0:00

በአራት ድንበሮች የሚዋሰኑት የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ድንበሮች የተቀሰቀሰው ግጭት እስከ ትናንት ምሽት ድረስ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል ።

ትናንትናና ከትናንት በስቲያ በነገሌ ቦረና አቅራቢያ በሚገኙ አምስት የቀበሌ ገበሬ ማኅበራት “ጦርነት” የመሰለ ግጭት መፈጠሩንና ከሶማሌ ክልል መጡ ባሏቸው “ልዩ ኃይል” ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

የጉጂ ዞን የፀጥታ ኃላፊ አቶ አዶላ ሚየሶ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ፤ “ችግሩን በመንግሥትና በባሕላዊ መንገድ ለመፍታት እየሞከርን ነው። ጉዳዩ ድንበር ለማስፋት መሆኑ ይገባናል። ጉዳቱ ሕብረተሰቡ ላይ እንዳይደርስ እየሠራንበት ነው። ለመንግሥት ባለስልጣናትም አሳውቀናል። የመንግሥት ባለስልጣናቱም በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዳለብን ነው የነገሩን። ሀገሪቱን እያስተዳደረ የሚገኘው ኮማንድ ፖስትም በሰላማዊ መንገድ እንድንፈታው እየነገሩን ነው።” ብለዋል።

የሁለቱን ክልልሎች የድንበር ግጭት በተመለከት ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው የነበሩት የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ግጭቱን ለማብረድ መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብቶ እያረጋጋ መሆኑን ገለፀው ከሶማሌ እና ከፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየሠሩ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG