በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ሃረርጌ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ የሞትና የመቁሰል አደጋ ተከሰተ


ትናንት በምሥራቅ ሃረርጌ ቆርኬ በተባለ የሃሮማያ ቀበሌ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች እንደሞቱና 36 እንደቀሰሉ ተነገረ፡፡

ትናንት በምሥራቅ ሃረርጌ ቆርኬ በተባለ የሃሮማያ ቀበሌ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች እንደሞቱና 36 እንደቀሰሉ ተነገረ፡፡ ሕይወቸውን ያጡት ሰዎች የቆርኬ ቀበሌ የመብራት መስመር ይዘረጉ የነበሩ ሰራተኞችን ለማገዝ ከተሰበሰቡ ከፊሉ ናቸው ተብሏል፡፡ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ኦሮምኛ ክፍል ቃላቸውን የሰጡት የአካባቢው ነዋሪ አቶ አብደላ አሚን ከሞቱት መካከል አንድ ልጃቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከድሬዳዋ የመብራት ኃይል መሥሪያ ቤት እንደመጡ የተነገረው ዘጠኝ ሰራተኞች ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቅር ሌላ ነዋሪ አደጋው የደረሰው በጥንቃቄ ጉድለት መብራቱ ከዋናው ማሰራጫ ሳይጠፋ የኤሌክትሪክ ሽቦውን ያዙበመባላቸው ነው ብሏል፡፡

የቆርኬ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ መሀሙድ ዩሱፍ ጉዳቱ መድረሱን አረጋግጠው መንስዔው እየተመረመረ ነው ተብሏል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG