በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉጂ ዞን ውስጥ ሰባት ሰው በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸው ተነገረ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን በሊባን ወረዳ ጥቃት አድርሰው ሰባት ሰዎችን ገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ የኦሮምኛ ዝግጅት ክፍል ገልፀዋል።

ከፍ ያለ ወታደራዊ ትጥቅ እንደነበረው የተነገረው ኃይል አሁንም ከአካባቢው አለመራቁን ነዋሪዎቹ አመልክተው የመከላከያ ሠራዊቱ ጣልቃ ገብቶ ሁኔታውን ማረጋጋቱን አስረድተዋል።

ጥቃቱ መፈፀሙን ለቪኦኤ ያረጋገጡት የሊበን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዋሪዮ ጎልቻ ተገደሉ የተባሉት ሰዎች አዛውንቶችና ጎልማሶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

ስለተባለው ጥቃት የሶማሌ ክልል መንግሥት ያውቅ እንደሆነና ባለሥልጣናቱ የሚሉትን ለመጠየቅ ወደ ጂጂጋ ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ለዛሬ አልተሣካም።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጉጂ ዞን ውስጥ ሰባት ሰው በታጠቁ ኃይሎች መገደሉ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:04 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG