የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 7029 ለሚሆኑ ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።
አንድ ሰው በተገደለበትና ከሃያ በላይ ሰው ለአካል ጉዳት በተዳረገበት አሰላ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሣምንት በተፈጠረ ግጭት ውስጥ እጆቻቸው አሉ ብሎ የጠረጠራቸውን ሰዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማዪቱ ፖሊስ አስታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ደረጃዎች ሲካሄድ የቆየው የብሔር ብሔረሰብ “የወንድማማችነት የውይይት መድረክ” ውጤታማ እንደ ነበር የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ጽሕፍት ቤት አስታወቀ።
በአሰላ ከተማ ትናንት፣ ረቡዕ በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ ከሃያ በላይ መቁሰላቸውን የከተማዪቱ ፖሊስ አስታውቋል።
“ለግል ጥቅማቸው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ” ባሏቸው የሱማሌ ክልል አመራር አባላት አድርሰዋል ላሉት ችግር እና ሥቃይ ማዘናቸውንና ይቅርታም እንደሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ኡመር አስታወቁ:: የኦሮሞና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ወንድማማችነት ጉባዔ ዛሬ አዳማ ከተማ ላይ ተካሂዷል። በጉባዔው ላይ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራር አባላት፣ አባገዳዎችና ኡጋዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ከተለያዩ የየማህበረሰቡ ክፍሎች የተወከሉ ተሳታፊዎች ተሣትፈዋል።
“ለግል ጥቅማቸው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ” ባሏቸው የሱማሌ ክልል አመራር አባላት አድርሰዋል ላሉት ችግር እና ሥቃይ ማዘናቸውንና ይቅርታም እንደሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ኡመር አስታወቁ፡፡
አዲሱ የኦሮሚያ አመራር የተሰጠውን ትልቅ ኃላፊነት በመገንዘብ ለህዝብ ጥያቄ ተግቶ እንዲሠራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳሰቡ።
የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት /ጨፌ/ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር አድርጎ ሾመ።
ዕቃ ጭኖ ከአዲስ አበባ ወደ ጂቡቲ ይጓዝ የነበረ ባቡር ተገልብጦ አደጋ እንደ ደርሰበት ፓሊስ ገለፀ።
ሻሸመኔ ከተማ ውስጥ ነሐሴ 6/ 2010 “አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ፈጽመዋል፤ ሟችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ዘቅዝቀው ሰቅለዋል” የተባሉ የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈረደባቸው።
አውሮፕላኑ ሲወድቅ የተመለከቱ የዐይን እማኞች፣ ስለድምፅና ምስል መዛነፍ ይቅርታ እንጠይቃለን።
ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት ስብርባሪ ውስጥ የተገኘው የመረጃ ቋት ወይም ብላክ ቦክስ ለምርመራ ወደ ውጭ እንደሚላክ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የአይሮፕላን አደጋ ምርመራ ዳይሬክተር ኮሎኔል አምድዬ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የኢትዮጵያ አውሮፕላን የተከሰከሰበትን መንስዔ የሚያጠና ቡድን ዛሬ ሥራውን ጀመረ።
የአዲስ አበባ የጋራ መኖርያ ቤቶች እደላን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖርያ ቤቶችን ዕጣ ማውጣት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግ/ ተዋጊዎችን ለመቀበል ወደ ጉጂ የተጓዙት የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች ከሁሉም ወገኖች ጋር በመነጋገር ለአቀባበል ሥርዓቱ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተገለፀ።
የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሠብ ተቋሟዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ በጥናትና መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና መጅሊስ መካከል የነበረውን አለመግባባት ይፋታል የተባለውን ጥናት ውጤት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
በኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዩጵያ መንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለመሸምገል ተዋቅሮ የነበረው የአባ ገዳዎች እና ሀገር ሽማግሌዎች የዕርቅ ኮሚቴ ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሠራዊት አቀባበል ሊያደርግ ነው።
በኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የተዋቀረው የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች የዕርቅ ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ፣ የዕርቅ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት መደረጉን ገለፀ።
በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና ኦነግ መካከል የተዋቀረው የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች የዕርቅ ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ፣ የዕርቅ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት መደረጉን ገለፀ። በሰላም ሥምምነቱ የተኩስ እና ግጭት ማቆም ሥምምነት ቢደርስም ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እየሞቱ የተጠየቁት አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ፣ ችግሩን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን ስሞታ እየቀረበ እና
ተጨማሪ ይጫኑ