በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳው ተቃውሞ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖርያ ቤቶችን ዕጣ ማውጣት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።

ተቃዋሚዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአስተዳደራዊ ወሰኑ ውጪ አርሶ አደሮችን አፈናቅሎ አላግባብ የገነባቸውን የጋራ መኖርያ ቤቶች ህግን በመጣስ ማከፋፈል የለበትም ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

የአዲስ አበባ የጋራ መኖርያ ቤቶች በዕጣ ዕደላ አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት የወጣውን ዜናን ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል።

ሰልፈኞቹ በኮዬ ፈጬ፣ ቦሌ አራብሳ እና ሌሎች ከአዲስ አበባ አስተዳደራዊ ወሰን ውጪ የሆኑ አካባቢዎች አርሶ አደሮችን በማፈናቀል ነዋሪዎቹን ማስፈር የለበትም በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

በጅማ፣ ሆለታ፣ ሻንቡ፣ ከሚሴ ወሎ፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ዓወዳይ፣ አዳባ፣ ባሌ ሮቤ እና ሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳው ተቃውሞ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG