በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ


በአማራ ክልል ሰላማዊ ሰልፎ
በአማራ ክልል ሰላማዊ ሰልፎ

ላለፍት 7 ቀናት ሲያካሂዱት የነበረውን ፀሎተ ምህላ ያጠናቀቁት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ምዕመናን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ይፈፀማሉ ያሏቸው ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቤተክርስቲያኗን አንድነት ለማምጣት ያደረጉትን አስተዋፅዖ ያደነቁት የባህር ዳር ሀገረስብከት ሊቀ-ጳጳስ አቡነ አብርሃም በዚህ ረገድ ያደረጉትን አስተዋፆ እንዲቀጥሉና አሁንም ቤተክርስቲያኗን እንዲታደጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተመሣሣይ ሁኔታም በሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ወሎና ሰሜን ወሎም ወረኢሉ፣ መቅደላ፣ አምባሰል፣ ወልድያ፣ ላሊበላና ደብረብርሃንን ጨምሮ ከሃያ በላይ ከተሞች ውስጥ ሰልፎች መደረጋቸውንና ሁሉም በሰላም መጠናቀቃቸው ታውቋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:54 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG