በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የኢትዮጵያ የብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ጉዳይ


በአማራ ክልል ያለፈው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ወቅት “የቁጥጥር መላላት ነበር” የሚል ለክልሉ የትምህርት ቢሮም ለሃገር አቀፉ የፈተናዎችና ምዘና ኤጀንሲም የቀረበ ቅሬታ እንደሌለ የክልሉ የትምህር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በ228 የፈተና ጣቢያዎች ውስጥ ቁጥራቸው ወደ ዘጠና ሁለት ሺህ የሚጠጋ ተማሪዎች ፈተናውን “በጥብቅ ቁጥጥር” ዶ/ር ይልቃል ከሪፖርተራችን አስቴር ምሥጋናው ጋር ባሕር ዳር ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል።

በሌላም በኩል በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ አካባቢ ለመንግሥት ሰራተኞች የቤት መስሪያ የተሰጠው ቦታ “ለእኛ ይገባል” በሚሉ ወጣቶችና በፀጥታ ኃይሉ መካከል በተፈጠረ ግጭት የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

የሞቱትንና የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራ ክልል የኢትዮጵያ የብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:38 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG