አዲስ አበባ፣ ዋሺንግተን ዲ.ሲ —
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፎችና እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡
በተለይ በአማኑኤል፣ በደምበጫ፣ በቋሪት፣ በይልማና ዴንሳዪቱ አዴት ሰላማዊ ሰልፎች እንደነበሩ፣ ዳንግላ ላይ ውጥረት እንደነበረ የገለፁት የመኢአዱ መሪ እዚያው ዳንግላ ውስጥ “የታጠቁ የመንግሥት ኃይሎች በሰዉ ላይ ወከባ ሲያደርሱ ነበር” ብለዋል፡፡
በምሥራቅ ጎጃም በግንደ ወይኒ የጎንቻሲሶ-እነሴ ነዋሪዎች ትናንት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የወልቃይትን ጉዳይ አንስተው ባለሥልጣናቱ እንዳወያይዋቸውና መልስ ሊሰጡ ተቀጣጥረው መለያየታቸውንም አቶ አቶ ሙሉጌታ አክለው ገልፀዋል፡፡
ግጭት የተፈጠረበት ሥፍራ እንደሌለ የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አመልክተዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የትናንትና የዛሬን አዳርና ውሎ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሣካም፡፡
የአዲስ አበባን የዛሬ ውሎና የሰሞኑን የተፈጥሮ፣ የጤናና የፀጥታ ሁኔታ፤ እንዲሁም ሌሎች ዓለምአቀፍ ዜናዎችን ያካተተውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡