በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘመዶቻቸውን ሁኔታ ለማጣራት ቅሊንጦ እስር ቤት የሄዱ የቤተሰብ አባላት ድብደባና እሥራት እንደደረሰባቸው ገለጹ


ቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት ቃጠሎው ጊዜ
ቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት ቃጠሎው ጊዜ

ዛሬ ቅሊንጦ እስር ቤት የዘመዶቻቸውን ሁኔታ ለማጣራት የሄዱ የቤተሰብ አባላት ድብደባና እሥራት እንደተፈፀመባቸው ተናገሩ።

በእሥር ቤቱ የነበሩ እሥረኞች የትና እንዴት ባለ ሁኔታ እንደሚገኙ ፍንጭ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

ፖሊስ ደበደበን ያሉት ወደ እሥር ቤቱ ሲያመሩ አቃቂ ወንዝ ድልድይ አከባቢና ቃሊቲ ቶታል ማደያ አከባቢ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ክስተቱን በተመለከተ ከመንግሥት ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG