በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦፌኮ ተከሳሶች "ፍርድ ቤቱ ባለመብት አይደለም" አሉ


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

​​የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አራቱን ከፍተኛ የአመራር አባላት ጨምሮ ዓቃቤ ህግ በሽብር ወንጀል ክሥ የመሠረተባቸው 22 ተከሳሾች ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ከተከሳሾቹ የበዙት ጉዳዩን የያዘው ፍርድ ቤት ባለ መብት እንዳልሆነ ገልፀው ቃላቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ፍርድ ቤቱ ግን ክደው እንደተከራከሩ መዝግቧል።

ችሎቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል።

የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያኔው፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ተከሳሾች ዛሬ በፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደተ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው የሰጡት የእምነት ክህደት ቃል በውዝግብ የታጀበ ሆኗል።

በቀደመው ቀጠሮ ዓቃቤ ህግ ላቀረበላቸው ክስ መልስ ሰጪዎቹ ያቀረቡት መቃወምያ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጎ ስለነበረ ዛሬ ከተከሳሾቹ ይጠበቅ የነበረው የእምነት ክህደት ቃል ብቻ ነበር።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኦፌኮ ተከሳሶች "ፍርድ ቤቱ ባለመብት ኣይደለም" አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG