በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንሶ የተሠማራው መከላከያ ሠራዊት ቢወጣም አከባቢው አለመረጋጋቱን አንድ የሕዝብ ተወካይ ገለጹ


በኮንሶ አንዳንድ ቀበሌዎች ተሠማርቶ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ቢወጣም ከአከባቢው ወረዳዎች የተውጣጡ ታጣቂዎች ተተክተው በሁለት ቀበሌዎች እየተዋጉ ነው ሲሉ ከኮንሶ የሕዝብ ተወካዮች አንዱ ነኝ ያሉት አስታወቁ።

የሕዝብ ተወካዩ በተጨማሪ ለቀናት የወደቁ አስከሬኖችም እስከዛሬ ለማንሳት አልተቻለም ይላሉ።

የደቡብ ክልላዊ መንግሥት ቃል-አቀባይ ይህንን ያስተባብላሉ።ሕዝቡም እየተረጋጋ እና ወደ ዘውትር ውሎው እየተመለሰ ነው ብለዋል።

በኮንሶ የተፈጠረው ግጭት አስመልክቶ ከኮንሶ ሕዝብ 23 ተወካዮች መካከል አንዱ መሆናቸው የሚገልጹት አቶ ገመቹ ገልሴ በመሠረቱ የተቀየረ ነገር የለም ብለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በኮንሶ የተሠማራው መከላከያ ሠራዊት ቢወጣም አከባቢው አለመረጋጋቱን አንድ የሕዝብ ተወካይ ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

XS
SM
MD
LG