የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የኬንያ ጉብኝት የሁለቱን ሀገሮች የቆየ መልካም ግንኙነት ባለው ለማስቀጠል ሳይሆን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሻገር የተደረገ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ፡፡
በደቡብ ኦሮምያ በአዶላ ከተማ በፀጥታ ኃይሎችና በተቃውሞ ሰልፎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ ታወቀ፡፡
በቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጠልለው፣ የቆዩ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች፣ ዛሬ ተጠቃለው ወደ ቅጥር ግቢያቸው መመለሳቸው ተሰማ፡፡
እስከዛሬ በየአካባቢው ለደረሱ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭቶች ዋነኛው ምክንያት የመንግሥት አስተዳደር አካላት ድክመት ነው ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ እንደተከፈተ መታዘባቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛዪድ ራ’አድ አል ሁሴን አስታወቁ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጉት ጉብኝት የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች እንደነበሩ ከተገለፀና በቅርቡ ከተፈቱት መካከል ጥቂቶቹን አናግረዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሺነር ሰብዓዊ መብቶች የልማት እና የሰላም መሰረቶች ናቸው አሉ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አዲስ ካቢኔ በመሰረቱ፣ ከወትሮው የተለየ እንዳልሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተናገሩ፡፡
አንድ የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ መግባባትና የሽግግር መንግሥት አስተባበሪ ኮሚቴ የተሰኘ አካል ሀገር ውስጥ ሊካሂድ ላቀደው ጉባዔ የርዕሰ ብሄሩን ድጋፍ እንዳገኘ አስታወቀ፡፡
ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 114 ሰዎች መካከል ዛሬ ሁለቱ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ከእስር መፈታታቸው ታወቀ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ114 ተከሳሾችን ክስ ማቋረጡ ታወቀ፡፡ ከእነዚህም መካከል ሁለቱ የዋልድባ ገዳመ መነኮሳት እንደሚገኙባቸውም ተረጋግጧል፡፡
በአለፉት ሰባትና ሥምንት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የጫት ምርት ከእጥፍ በላይ መጨመሩን ታውቁ ነበር? ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ፣ ገቢውም በሦስት እጥፍ አድጓል፡፡
በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ መሾምና ባደረጉት ንግግር ላይ ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ ዘጋቢዎቻችን ከዚህም ከዚያም ከሕዝብ የሰበሰቧቸውን አስተያየቶች አድርሰውናል፡፡
በቅርቡ በኮንድ ፖስቱ ትዛዝ በባህርዳር ከተማ ታሥረው የነበሩ 19 ትጠርጣሪዎች ዛሬ ረፋዱ ላይ መፈታታቸው ታወቀ፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር አመስግነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ዶ/ር አብይ አህመድን በሊቀመንበርነት በመምረጡ መደሰታቸውን አንድ የቀድሞ የፓርላማ አባል ተናገሩ፡፡
ገዥው ግንባር ኢህአዴግ አዲስ ሊቀመንበር መሰየሙ ተስፋ የፈነጠቀ እንደሆነ ጥቂት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የአዲስ ሰዎች መመረጥ ብዙ ለውጥ እንደማያመጣም የተናገሩም አሉ፡፡
በንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የእነ እስክንድር ነጋ አያያዝ ከመሻሻል ይልቅ እየተበላሸ እንደሄደ የጎበኟቸው ሰዎች ተናገሩ፡፡
ዓቃቤ ሕግ ከዋልድባ ገዳም ተይዘው በእሥር በሚገኙት ሁለት መነኮሳት ላይ እንዲመሰክሩ ቆጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ምስክሮች ዛሬ ሳያቀርብ ቀረ፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ የዜጎችን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ በማፈን የአገዛዙን ሥርዓት በኃይል ማስቀጠል አይቻልም ሲል መግለጫ አወጣ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ