አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ እንደተከፈተ መታዘባቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛዪድ ራ’አድ አል ሁሴን አስታውቀዋል።
የተቀሰቀሰውን የለውጥ ፍላጎት ማርካት ለመንግሥቱ ታላቅ ፈተና እንደሚሆን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መናገራቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኮሚሽነሩ በጉብኝታቸው ማብቂያ ባሠራጩት መግለጫ ይህንኑ የሕዝብ ተስፋና ሥጋት አስተጋብተዋል፤ ‘በአስቸኳይ ሊወሰዱ ይገባል’ ያሏቸውን እርምጃዎችም ጠቁመዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ