85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያን አርሶ አደርና አርብቶ አደር የዝናብ ውሃን ጠብቆ ነው የሚተዳደረው። በየአመቱ በሚዘንበው የዝናብ መጠን ማነስ ከአምራች ገበሬዎቹ ህይወት በተጨማሪ በምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ እጥረት ይገጥማል።
ሳሙአል መርጋ ይባላል። እድሜው 17 ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። በመደበኛ ትምህርቱ የከፍተኛ ውጤት ተሸላሚ ነው።የተለያዩ ቅርፅ ያላቸው ትንንሽ ተንቀሳቃሽ ሮቦቶችን ሰርቷል በመስራትም ላይ ይገኛል።
በርካታ ሰዎች በተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች በሚገኙ በፍጥነት ከፍና ዝቅ እያሉ በሚምዘገዘጉ ተሽከርካሪ መሰል የሮለር ኮስተርስ (Roller Coasters) ይዝናናሉ። ለአዲሱ ትውልድ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሰራው Roller Coasters በምናብ የሚያሳዩ ታምራዊ የእይታ ቴክኖሎጂዎች ተገጥሞላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በሰሜን አሜሪካ በሚገኘው ቲም ፓርክ (Theme Park)፣ በአውሮፓና በእስያ አዲሶቹ የቴክኖሎጂ ግኝቶች በግልጋሎት ላይ ውለዋል።
በቪዠን ኢትዮጵያና በኢሳት መጋቢት 17 የተዘጋጀ የሦስት ፓርቲዎች ውይይት ኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና የብሔራዊ አንድነት መንፈስን ለማጠናከር በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቪዥን ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን (ኢሳት)አዘጋጅነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ቅዳሜ መጋቢት 17 እና እሁድ መጋቢት 18 የሁለት ቀን ውይይት ተካሂዶ ነበር።
የኢህአዴግ መንግሥት ባአሁኑ ጊዜ ሕዝባዊ ተቃውሞን ለመጨፍለቅ የሚወስደው እርምጃ ከፋሽስቶች ጭካኔ አይተናነስም ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ከሷል። የኢህአዴግ እርምጃ ከማሰርም አልፎ እንደ ደርግ ዘመን የገደለውን አስከሬን በየቦታው እስከመጣል ደርሷል ብሏል። አገሪቱን ወደ ተሻለ አቅጣጫ ለመምራት ኢህአዴግ ከመድረክ እና ሌሎች ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካላቸው ጋር ባስቸኳይ እንዲደራደርም ጠይቋል።
“የጨው ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልጥ ያለቅሳል፤ እንደሚባለው አሁን ያለው ሁኔታ እኔ ያሳስበኛል።” ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ። “አደገኛ ሁኔታ ነው። ... ምን ዓይነት ለውጥ? ... ዕድልም አደጋም የያዘ አጋጣሚ የያዘ ነው፤ የሚመስለኝ።” አቶ ፈቃደ ሸዋቀና።
በዘንድሮው የኒው ዮርኩ የሥነ ጥበብ፥ የደቡብ አፍሪቃ፥ የኬንያ፥ የናይጄሪያና የአይቮሪኮስት ታዋቂና ወጣት ባለ ሞያዎች፥ የተለያዩ የሥነ ጥበብ ማሳያዎች ባለቤቶችና እንዲሁም የጥበብ ዘርፉ አዋቂዎች ተገኝተዋል።
ከተጀመረ አምስተኛ ወሩን ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀረው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞ በአንዳንድ ከተሞች በሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ከትናንት በስቲያ፣ ትናንትና ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማና ደባዩ በተባለ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት እንዲሁም በበደሌ ከተማና ለሊሳ ሃሮ ቶሬ በተባለች የገጠር ቀበሌ ተማሪዎች እንደታሠሩና በአስለቃሽ ጭስ ምክንያት፤ ሆስፒታል እንደገቡ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
እ.አ.አ 1985 ዓ.ም በተሰራው የሆሊውድ ፊልም ባክ ቱ ዘ ፊውቸር “Back to the Future” ለማሳየት የሞከረው የወደፊት ቴክኖሎጂ እውን የሆነ ይመስላል። በፊልሙ ውስጥ ማርቲ ማክፍላይ (Marty McFly) በማክል ጄ ፋክስ (Michael J. Fox) የተተወነው ገፀባህሪ የሚለብሰው ጫማ ራሱን በራሱ እግር ፈልጎ ጥልቅ ይልና፤ ያስርም ነበር።
ሳልሳ የሙዚቃ ስልት ስረ መሰረቱ ከኩባና በውሃ ከተከበበችው ደሴት ፖርተሪኮ ነው። የሳልሳ ሙዚቃ ለነዚህ ሁለት ሃገሮች መገለጫቸው የሆነ የባህላዊ የዳንስ ሙዚቃ ነው።
ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ዋሽንግተን ውስጥ ባዘጋጁት የሁለት ቀን ጉባኤ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር "ሽግግር፣ ዴሞክራሲና ብሔራዊ አንድነት” በሚለው የውይይት ርእስ ሥር፤ የሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችና የማኅበራት አደረጃጀቶች፤ ግጭቶችን በመፍታትና ዴሞክራሲን በማስፈን ረገድ ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚናና ከግጭቶች መርገብ በኋላ በሚኖረው የሽግግር ወቅት ምን ይጠበቅባቸዋል?በሚል ርእስ አራት ተወያዮች ጹሑፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡
“‘ኮሌስትሮል’ ሲባል ሁሌ እንደ መጥፎ ነገር የማየት ዝንባሌ አለ። በመሠረቱ ያለ ‘ኮሌስትሮል’ ሕይወት የለም። ኮሌስትሮል ጠቃሚም ነው፤ መጠኑ ሲበዛ ደግሞ ለአደጋ የሚዳርግ ይሆናል።” የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ።
ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ባደረገው ጥናት መሰረት በአለማችን ከሚከሰቱት ድንገተኛ ሞት በአመት 12.6 ሚልየን የሚሆነው ጤናማ ባልሆኑ የአካባቢ ንብረት መበረዝ ምክንያት እንደሆነ ተረጋግጧል።
ማይክሮሶፍት የተባለው አለም-አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት እ.አ.አ 2015 ዓ.ም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት “ማይክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ” በሚል ስያሜ በናይሮቢ ኬንያ ከፍቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ