በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊቷ አምሮት አብደላ ’ማክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ’ን እንድታስተዳድር ተሾመች!


ፋይል-ፎቶ አምሮት አብደላ
ፋይል-ፎቶ አምሮት አብደላ

ማይክሮሶፍት የተባለው አለም-አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት እ.አ.አ 2015 ዓ.ም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት “ማይክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ” በሚል ስያሜ በናይሮቢ ኬንያ ከፍቷል።

‘ማክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ’ የተባለውን ቅርንጫፍ በናይሮቢ ኬንያ የተከፈተበት ዋናው ምክንያት የአፍሪካ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና አፍሪካን በቴክኖሎጂ ፈጠራም ሆነ አጠቃቀም ካደጉት ሃገሮች ጋር በእኩል ለማራመድ ነው። ለዚህ ቅርንጫፍ መ/ቤት የማስተዳደሩን ስራ ሙሉ በሙሉ እንድታከናውን ኢትዮጵያዊቷ አምሮት ዓብደላ ተሾማ በመስራት ላይ ትገኛለች። አምሮት ከአሁን በፊት በዚህ ድርጅት በተለያዩ ዘርፎች ከዚሁ መስሪያ ቤት ጋር ለሶስት ዓመታት ሰርታለች።

የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ አሁን በስፋት በኬንያ፣ ደቡብአፍሪካ፣ አይቮሪኮስት፣ታንዛንያ፣ሩዋንዳ፣ኡጋንዳ፣ ሞውሪሽየስ፣ ናይጄሪያና ጋና ውስጥ በመሥራት ላይ ይገኛል። እስከ አሁን የተኘውን ውጤታማነት በተመለተከተ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ አምሮት አብደላ ስትገልፅ ድርጅቱ እንደበጎ-አድራጊ ድርጅት መስጠት ብቻ ሳይሆን በገንዘብ ትርፍማ መሆን ይፈልጋል። በአሁኑ ሰአት ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የቴክኖሎጂ ለውጥ ለማምጣት የማስተዋወቁ ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑንና በትምህርትና በጤና አገልግሎት ረገድ ቴክኖሎጂ የሚጫወተውን ሚና በመገንዘብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን አስረድታለች።

የማይክሮ ሶፍት ዳይሬክተር አምሮት አብደላ በማጠቃለያ ድርጅቱ በሁሉም አፍሪካ ሃገራት ቴክኖሎጂን የማስተዋወቅ፣ አፍሪካውያንን የበለጠ በቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግና በፈጠራ ስራ ወጣቶችን ማሳተፍ ዋና አላማው እንደሆነ ገልፃለች። ይህንን እቅድ ለማሳካትም ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት የመንግስታትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ትብብር በእጅጉ እንደሚያስፈልግ አክላ ተናግራለች።

ኢትዮጵያዊቷ አምሮት አብደላ ’ማክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ’ ን እንድታስተዳድር ተሾመች!
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG