በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአለማችን የአየር ንብረት ብክለት በርካታ የሰው ልጅ ህይወትን እየቀጠፈ ነው


ፋይል-ፎቶ የአለም የጤና ድርጅት (World Health Organization)
ፋይል-ፎቶ የአለም የጤና ድርጅት (World Health Organization)

ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ባደረገው ጥናት መሰረት በአለማችን ከሚከሰቱት ድንገተኛ ሞት በአመት 12.6 ሚልየን የሚሆነው ጤናማ ባልሆኑ የአካባቢ ንብረት መበረዝ ምክንያት እንደሆነ ተረጋግጧል።

ጥናቱ እንደሚያመለክተው የአየር፣ የውሃና አፈር መበረዝ፣ ኬሚካል ፍሳሽ፣ የአየር ለውጥ እና በአደገኛ ጨረር ምክንያት የአካባቢ አየር ንብረት ተበክሏል በዚህም ከመቶ በላይ የሚሆኑ የበሽታ አይነቶችና የሰውነት ጉዳቶች ደርሰዋል። በተለይም የሰሜን ምስራቅ እስያ እና የምዕራብ ፓስፊክ አካባቢዎች በነዚህ ዋንኛ ችግር ምክንያት የሰው ልጅ ሞት ቁጥር ተበራክቷል።

ከአስርት አመታት በፊት የሰው ልጅን ለሞት የሚያበቁት በሽታዎች እንደ ተቅማጥ፣ ወባ እንዲሁም የንፁህ ውሃ እጥረትና ከቁሻሻ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎች ነበሩ።

ካለፈው አስር አመት ወዲህ ግን በነዚህ ምክንያቶች የሚከሰቱ በሽታዎች በእጅጉ ቀንሰዋል፣ የተጣራ ውሃ በስፋት በመዳረሱና የተሻለ የቁሻሻ ማስወገጃ ዘዴዎች መጠቀም በመቻላችን ምክንያት። አሁን እየደረሰ ያለውን የተፈጥሮ መዛባትን ባለመረዳትና አስቀድሞ መፍትሄ ባለመበጀቱ አለማችን ለከፍተኛ ችግር ተዳርጋለች።

የWHO የአካባቢ ጤና ሃላፊ ማሪያ ኔይራ (Mria Neira) እንዳሉት 8.2 ሚልየን የሚሆነው የሰው ልጅ ህይወቱን የሚያጣው በአየር ብክለት ምክንያት በተከሰተ በሽታ ነው፣ እንደቀላል የምናየው የሲጃራ ሽታን ጨምሮ።

እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ዘገባ በአንጎል ውስጥ የደም ቧንቧ ሲዘጋ የሚፈጠረውን የህመም በሽታ፣ የልብ ህመም፣ ካንሰር እንዲሁም ስር የሰደዱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች 2/3 ኛ ለሚሆነው የአለማችን ሞት ምክንያት ሆኗል። ናይራ ለVOA ዘጋቢያችን እንዳስረዱት ለበሽታው ህክምና ከሚወጣው ገንዘብ ለአየር ንብረቱ ደህንነት የሚውለው ገንዘብ መጠን በእጅጉ ያነሰ ነው።

ለአየር ንብረቱ ጥበቃ ሲባል እንዲሁም በአየር ብክለቱ ምክንያት የሚከሰቱትን በሽታዎች ለመቀነስ በጤና ላይ ችግር የማያመጡ መገልገያዎችን ለምሳሌ በነፋስ እና በፀሃይ ብርሃን የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ለየእለት ግልጋሎት በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል። የንፁህ ውሃ አቅርቦትን፣ የተሻለ የቁሻሻ ማስወገጃ ዘዴዎች መጠቀም፣ እንዲሁም አዳዲስ የሚገነቡ ቤቶች ሃይል ቆጣቢ ሆነው ቢሰሩ የተሻለ ነው ሲል አለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO አሳስቧል።

የቪኦኤዋ ባልደረባችን ሊሳ ስቼሊየን ከጄኔቫ የዘገበችውን መስታወት አራጋው ታቀርበዋለች። ከበታች የለውን የድምፅ ምልክት በመጫን አጠር ያለ ዘገባውን መስማት ይችላሉ።

የአለማችን የአየር ንብረት ብክለት በርካታ የሰው ልጅ ህይወትን እየቀጠፈ ነው!
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG