እ.አ.አ 1985 ዓ.ም በተሰራው የሆሊውድ ፊልም ባክ ቱ ዘ ፊውቸር “Back to the Future” ለማሳየት የሞከረው የወደፊት ቴክኖሎጂ እውን የሆነ ይመስላል። በፊልሙ ውስጥ ማርቲ ማክፍላይ (Marty McFly) በማክል ጄ ፋክስ (Michael J. Fox) የተተወነው ገፀባህሪ የሚለብሰው ጫማ ራሱን በራሱ እግር ፈልጎ ጥልቅ ይልና፤ ያስርም ነበር።
ሳልሳ የሙዚቃ ስልት ስረ መሰረቱ ከኩባና በውሃ ከተከበበችው ደሴት ፖርተሪኮ ነው። የሳልሳ ሙዚቃ ለነዚህ ሁለት ሃገሮች መገለጫቸው የሆነ የባህላዊ የዳንስ ሙዚቃ ነው።
ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ዋሽንግተን ውስጥ ባዘጋጁት የሁለት ቀን ጉባኤ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር "ሽግግር፣ ዴሞክራሲና ብሔራዊ አንድነት” በሚለው የውይይት ርእስ ሥር፤ የሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችና የማኅበራት አደረጃጀቶች፤ ግጭቶችን በመፍታትና ዴሞክራሲን በማስፈን ረገድ ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚናና ከግጭቶች መርገብ በኋላ በሚኖረው የሽግግር ወቅት ምን ይጠበቅባቸዋል?በሚል ርእስ አራት ተወያዮች ጹሑፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡
“‘ኮሌስትሮል’ ሲባል ሁሌ እንደ መጥፎ ነገር የማየት ዝንባሌ አለ። በመሠረቱ ያለ ‘ኮሌስትሮል’ ሕይወት የለም። ኮሌስትሮል ጠቃሚም ነው፤ መጠኑ ሲበዛ ደግሞ ለአደጋ የሚዳርግ ይሆናል።” የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ።
ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ባደረገው ጥናት መሰረት በአለማችን ከሚከሰቱት ድንገተኛ ሞት በአመት 12.6 ሚልየን የሚሆነው ጤናማ ባልሆኑ የአካባቢ ንብረት መበረዝ ምክንያት እንደሆነ ተረጋግጧል።
ማይክሮሶፍት የተባለው አለም-አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት እ.አ.አ 2015 ዓ.ም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት “ማይክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ” በሚል ስያሜ በናይሮቢ ኬንያ ከፍቷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጅኒያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሃገርን ቅርስ ባህልና ታሪክ በማስጠበቅና በማሳወቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።
“የመገናኛ ብዙሃን ለቋንቋ እድገትም ሆነ መቀጨጭ አስተዋፆ አለው፡ ጋዜጠኛም ሆነ ፀሃፊ በቋንቋው ላይ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል” ይላል እንግዳችን አቤል አዳሙ።
ከተመሰረተ ከአራት አመት ተኩል በላይ የሆነው የጃኖ ባንድ አራት ድምፃውያንና ስድስት የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች የያዘ ነው።
እንግሊዛውያኑ ወጣት ሮሊንግ ስቶንስ (Rolling Stones) እ.አ.አ በ1960ዎቹ በሮክ ኤንድ ሮል (Rock & Roll) የሙዚቃ ስልት የተለየ አድማጭ ያገኙ ተወዳጅ ሙዚቀኞች ነበሩ።
እሁድ ዕለት በኮንሶ ደበና በተባለች መንደር ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን የሟች ሞሌ አዛዥ አባትና የሟች ፋንታዬ ጊዮርጊስ አጎት ተናግረዋል።ወደ 55 ሺሕ የሚኾኑ ነዋሪዎች ተፈራርመው ኮንሶ ከወረዳ ወደ ዞን ከፍ እንዲል ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት፤ ጥያቄውን ለመንግሥስት ካቀረቡት የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ መታሠራቸውን ሌሎች ደግሞ በስጋት ተሸሽገው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ጽዮን ግርማ የሟች ቤተሰቦችንና የኮሚቴውን አባላት አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች፡፡
“ከዚህም የከፋ ነገር በየእሥር ቤቱ ይፈጸማል” የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ መርማሪና የሕግ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም በደቡብ ኦሞ ስለሚፈጸሙ የመብት ጥሰት ይናገራሉ፡፡
ለጥያቄዎ መልስ በተሰኘው የትላንቱ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአድማጮች ለተነሱ ጥያቄዎች ምሑራን መልስ ሰጥተውበታል። “ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች መኾኑ እየተነገረ እንዴት ረሃብ ይከሰታል?” ለሚለው ጥያቄ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ዶክተር መሐሪ ረዳኢ መልስ ሲሰጡ ነበር ፕሮግራማችን ያበቃው፤ ዛሬ ከቆመበት ይቀጥላሉ።
በ1960ዎቹ ሴት ልጅ በአደባባይ መውጣት ባልተለመደበት ዘመን ፤ ደስታ ሃጎስ የራስዋን የስዕል ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ያዘጋጀች የመጀመሪያዋ የሴት ሰአሊ። ባሳለፈችው የጥበብ ስራ ዘመን ከሃምሳ ጊዜ በላይ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለብቻዋና ከሌሎች ሰአሊዎች ጋር በጋራ በመሆን ለእይታ አቅርባለች።
ተጨማሪ ይጫኑ