ዋሽንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና የብሔራዊ አንድነት መንፈስን ለማጠናከር በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቪዥን ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን (ኢሳት) አዘጋጅነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ቅዳሜ መጋቢት 17 እና እሁድ መጋቢት 18 የሁለት ቀን ውይይት ተካሂዶ ነበር።
በዚህ ውይይት ስድስት የተለያዩ ርእሶች ቀርበው ምሑራን፣የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮችና ግለሰቦች ሐሳባቸውን አቅርበው ተወያይተዋል፡፡
ቅዳሜ መጋቢት 17 መጨረሻ ላይ በነበረው ውይይት ሦስት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጹሑፎቻቸውን አቅርበው ተወያይተዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት የዚህ ውይይት የመጀመሪያ ክፍል ተላለፎ ነበር፡፡
ውይይቱን የተከታተለችው ጽዮን ግርማ ዘገባ ሁለተኛው ክፍል ዛሬ ይቀጥላል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡