በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባክ ቱ ዘ ፊውቸር የተሰኘው ፊልም ላይ የነበረው ታምራዊ ጫማ እውን ሆነ!


ፋይል-ፎቶ የናይክ አዲሱ ጫማ
ፋይል-ፎቶ የናይክ አዲሱ ጫማ

እ.አ.አ 1985 ዓ.ም በተሰራው የሆሊውድ ፊልም ባክ ቱ ዘ ፊውቸር “Back to the Future” ለማሳየት የሞከረው የወደፊት ቴክኖሎጂ እውን የሆነ ይመስላል። በፊልሙ ውስጥ ማርቲ ማክፍላይ (Marty McFly) በማክል ጄ ፋክስ (Michael J. Fox) የተተወነው ገፀባህሪ የሚለብሰው ጫማ ራሱን በራሱ እግር ፈልጎ ጥልቅ ይልና፤ ያስርም ነበር።

በቅርቡ Nike በመባል የሚታወቀው የጫማ አምራች በፊልም ላይ ብቻ የሚታወቀውን ጫማ እውን አድርጎታል።

ሃይፐር አዳፕት 1.0 (HayperAdapt 1.0) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ለዚህ አዲስ ቴክኖሎጂ ለሆነው ጫማ። ልክ እግር ወደ ጫማው እንደገባ ጫማው እራስ በራሱ መታሰር ይጀምራል። ለምናልባቱ የተጫማው ሰው አጠበቀኝ ወይም ላላብኝ እንዳይል ጫማውን ለማጥበቅና ለማላላት ሁለት መቆጣጠሪያም ተበጅቶለታል።

የጫማው አምራች ኩባንያ ናይክ እንዳስረዳው፤ የዚህ ጫማ ቴክኖሎጂ ናይክ ማግ (NIKE MAG) ከተሰኘው ጫማ ጋር ለአመታት እንዴት ወደስራ እንደሚውል ሲጠናበት ቆይቷል።

አዲሱ ጫማ በሶስት አይነት ቀለሞች ምርጫ በቅርቡ በሚከበሩት የፈረንጆቹ በአላት ላይ ለገበያ ይቀርባል ተብሎም እቅድ ተይዞለታል።

የጫማው ዲዛይነር ቲንከር ሃትፊልድ (Tinker Hatfield) ለሲኤን ኤን (CNN) ዘጋቢ እንዳስረዳው፤ ጫማው የተሰራበት ዋናው ምክንያት ለስፖርተኞች ምቾትና ቅልጥፍና ይረዳ ዘንድ ነው።

"የሚያስፈልግ እድገት ነው፤ ምክንያቱም በስፖርት ውድድር ወቅት እግር ከፍተኛውን ሚና ስለሚጫወት።" በማለት ተናግሯል ዲዛይነር ቲንከር ሃትፊልድ። ዘገባው የCNN ሲሆን መስታወት አራጋው በአጭሩ አቀናብራዋለች። ከበታች ያለው የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።

ባክ ቱ ዘ ፊውቸር(Back to the Future) የተሰኘው ፊልም እና የናይክ( Nike) ጫማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG