በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!


ፋይል-ፎቶ ሳሙኤል መርጋ
ፋይል-ፎቶ ሳሙኤል መርጋ

ሳሙአል መርጋ ይባላል። እድሜው 17 ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። በመደበኛ ትምህርቱ የከፍተኛ ውጤት ተሸላሚ ነው።የተለያዩ ቅርፅ ያላቸው ትንንሽ ተንቀሳቃሽ ሮቦቶችን ሰርቷል በመስራትም ላይ ይገኛል።

አባቱ አቶ መርጋ ነገራ የሳሙኤልን የልጅነት ፍላጎት በመመልከት ስዕል መሳል እንዲማር ያበረታቱት ነበር። በተለይም የመጀመሪያው የሆነችው የሂሊኮፕተር ስዕል እንድትንቀሳቀስ ልዩ ፍላጎት ያደረበት ሳሙኤል በአጠገቡ ያገኛቸውን ቁሳቁሶች በመጠቀም ወደ ቅርፅነት ቀጥሎም በኤሌክትሪክ በመታገዝ እንድትንቀሳቀስ አድርጓታል።

ሳሙኤል መርጋ በርካታ ትናንሽ ሮቦቶችን ሰርቷል። እንዚህን ትናንሽ ሮቦቶች ጨርሶ ለመስራት ረጅም ጊዜ እንደማይወስድበትም ይናገራል። የወደፊት እቅዱም የሚፈጥራቸው ሮቦቶች ለሰው ልጆች የስራ እገዛ ይውሉ ዘንድ ነው።

ሌላው የሳሙኤል መርጋ የወደፊት አላማ በምርምርና በፈጠራ ስራ በትምህርቱ በከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ በአለም አቀፍ ደረጃም ሮቦቶችን መስራትና ተመራማሪ መሆን ነው።

ስራውን ከጅምሩ በማበረታታትና በሃሳብም ሆነ በቁሳቁስ በመደጎም ከሳሙኤል ጎን የማይለዩት አባቱ አቶ መርጋ ነገራ እና እናቱ ወ/ሮ ጌጤ ጋቢሳ የልጃቸውን ፍላጎት ለሟሟላት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ልጃቸው የወደፊት ህልሙ እውን ይሆን ዘንድ ከኛ የተሻለ የቁሳቁስም ሆነ የእውቀት እርዳታን ያሻዋል ይላሉ።

ከህፃንነቱ ጀምሮ በሃሳብ ከጎኑ ያልተለዩትና የሳሙኤል የቤተሰብ አካል የሆኑት ነብዩ አዱኛ በመጨረሻ "ሳሙኤል የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ቢያገኝ የበለጠ መስራት የሚችል አዳጊ ወጣት ነው፡ ሁላችንም በምንችለው ከጎኑ መቆም አለብን” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል።

ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!
ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!

ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!
ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!

ኢትዮጵያዊው ወጣት ሮቦት ፈጣሪ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:06 0:00

XS
SM
MD
LG