ከዚህ ቀደም የነበረው በአዲስ ሞዴል ተቀይሮ የሳምሰንግ (Samsung) የጆሮ ማጉሊያ በተጨማሪ ተገጥሞለታል፤ ከሳምሰንግ ስልክ ጋር የተያያዘ መነፅርም አለው።
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ አቅጣጫን የሚጠቁም ሳጥን የተገጠመለት ሲሆን የመዝናኛው ተሽከርካሪ ወዴትም ቢዟዟር ቦታውን በትክክል ይጠቁማል። እንዲሁም በአይን የሚታየውን የሚገልፅ ገመድ አልባ መዳመጫ ተያይዞለታል።
አምራች ኩባንያው እንደገለፀው ሁሉም የሮለር ኮስተርስ (Roller Coasters) እንደዚህ አዲሰ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ምናባዊ እይታ የሚሰጠውን ደስታ ላይሰጥ ይችላል።
አዳዲሶቹ ሮለር ኮስተርስ ከነሃስ ነው የተሰሩት። በቀላሉ የሚታዘዙ እንዲሁም በሰማይ ላይ በምናብ ከተፈጠረው ከተማ ውስጥ ከሌላ አለም ፍጡራን ጋር የሚያዝናና ግጥሚያ እንዲያደርጉ ይረዳሉ።
በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ናይን ሲክስ ፍላግስ (Nine Six flags) የመዝናኛ ቦታ በዚህ አመት አዲሱን የምናባዊ እውነት ቴክኖሎጂን ለመዝናኛነት ለተጠቃሚ ያቀርባል። ትግልንና አዲስ ነገርን ለሚወዱት ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው በጣም የተለየም ነው።
ዘጋቢያችን ኤልሳቤጥ ሊ (Elisabeth Lee) በስፍራው ተገኝታ ከነኚህ ድንቅ ግኝቶች በአንዱ ተሳፍራ ያጠናቀረችውን ዘገባ መስታወት አራጋው ይዛ ቀርባለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ።