ዋሽንግተን ዲሲ —
ያነጋገርናቸው ሁለት ሰዎች ቤተሰቦቻቸው እንደታሰሩባቸው፣ በኮንሶ የተነሳውን በዞን የመደራቸት ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ጫካ መግባታቸውንና እየተፈጠሩ ባሉት ሁኔታዎች ግራ እንደተጋቡ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
የደቡብ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልላቸውም ስልካቸውን ሊያነሱልን ባለመቻላቸው ልናገኛቸው አልቻልንም።
በተመሳሳይ ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም ልናገኛቸው አልቻልንም።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።