በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንሶ ሕዝብ በዞን እራሱን በራሱ ለማስተዳደር ጥያቄ አቀረበ


ፋይል ፎቶ - የኮንሶ ገበሬዎች ዘር እየዘሩ [የአሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ/AP]
ፋይል ፎቶ - የኮንሶ ገበሬዎች ዘር እየዘሩ [የአሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ/AP]

የደቡብ ክልል ብሄር ብሔረሰብ አስተዳደር ባለስልጣናት የዞን ጥያቄዉ አይፈቀድም ከማለታቸዉም በላይ በእስራትና ሕዝቡን እንያገሉቱት ነዉ ብለዉናል።

የኮንሶ ሕዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር ያቀረበዉ የዞን ጥያቄ በክልሉ ባለስልጣናት ተቀባይነት ያለማግኘቱን ተከትሎ ባለስልጣናት ልዩ ወታደራዊ ሃይል አስፍነዉብናል ይላሉ፣ ከአካባቢዉ ወደ አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ስልክ የደወሉ።

የሃምሳ ሺህ 33 አካባቢዉ ሕዝብ የፈረመዉና ፊርማዎችን አሰባሰበዉ በቀበሌዎችና በወረዳ ምክር ቤት የጸደቀ የዞን ጥያቄ ተቀባይነት እንዳላገኘ ሕዝቡ የወከለዉ ነዉ የተባለ ኮሚቴ አባል ገልጸዉልናል።

የደቡብ ክልል ብሄር ብሔረሰብ አስተዳደር ባለስልጣናት የዞን ጥያቄዉ አይፈቀድም ከማለታቸዉም በላይ በእስራትና ሕዝቡን እንያገሉቱት ነዉ ብለዉናል።

ላለፉት በርካታ ቀናት ባለስልጣናቱን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት ግን አልተሳካም፥ የክልሉን ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ክፍሌ ገብረ ማሪያምን ለማናጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገን ነበር ስልካቸዉ አይነሳም፥ የክልሉ አፈ ጉባኤ አቶ ለማ ገዙማ ግን ስብሰባ ላይ ሰለሆኑ መልሰን እንድንደዉል ነገረዉን፥ መላልሰን ብንደዉል ልናገኛቸዉ አልቻልንም፣ ወደፊት ጥረታችንን እንቀጥላለን።

ኮንሶ ስላለበት ሁኔታ ግን ሕዝቡን ወክለዉ ኮሚቴ አባል አቶ ገመቹ ደንፌ ትዝታ በላቸዉን አነጋግረዋል። ዝርዝሩን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

የኮንሶ ሕዝብ በዞን እራሱን በራሱ ለማስተዳደር ጥያቄ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:24 0:00

XS
SM
MD
LG