በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በኮንሶ ዐሥር ሰው እንኳን ለተቃውሞ ወጥቶ አያውቅም” አቶ ፍሰሃ ጋረደው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር


yared hailemariam
yared hailemariam

“ከዚህም የከፋ ነገር በየእሥር ቤቱ ይፈጸማል” የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ መርማሪና የሕግ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም በደቡብ ኦሞ ስለሚፈጸሙ የመብት ጥሰት ይናገራሉ፡፡

ካለፈው እሁድ ጀምሮ በደቡብ ክልል በኦሞ ዞን የሚገኙ አራት ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ፣ እግር ለእግርና አንገት ለአንገት በቃጫ ገመድ ታሥረውና እንግልት ደርሶባቸው የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በማኅበራዊ ሚድያ ስለመለቀቃቸው፣ ስለኮንሶ ሕዝብ አቤቱና ሲዳማ አርነት ፓርቲ በሲዳማ እየተፈጸመ ነው ሰላለው የመብት ጥሰት የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ፍስሃ ጋረደው ተጠይቀዋል፡፡በደቡብ ኦሞ ስለታየው ፎቶ በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት እንደሚያጣሩ ሲገልጹ በኮንሶ ግን ምንም ተቃውሞ የለም ሰላም ነው ብለዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ መርማሪና የሕግ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያምን ፤” በዚህ ዘመን መሐል ከተማን በሕንጻ እያሸበረቁ፤ ኢትዮጵያ አድጋለች የሚባለው እነዚህ ሰዎች ተረስተው ነው” ይላሉ፡፡

ሁለቱንም ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ

“በኮንሶ ዐሥር ሰው እንኳን ለተቃውሞ ወጥቶ አያውቅም” አቶ ፍሰሃ ጋረደው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG